የፕላስቲክ ቄጠማ ምርትና ስርጭት ይታገድ!

የፕላስቲክ ቄጠማ ምርትና ስርጭት ይታገድ!
The Issue
ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
ለኢፌድሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
ለኢፌድሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
ለኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር
ለኢፌድሪ ግብርና ሚኒስቴር
ለኢፌድሪ ፕላን ሚኒስቴር
ለኢፌድሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
እኛ፣ ከዚህ በታች ስማችን የተዘርዘረው ኢትዮጵያውያን፣ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በሃገራችን እየተስፋፋ የመጣውን አርቲፊሻል የፕላስቲክ ቄጠማ ምርቱና ስርጭቱ በእጅጉ እየተስፋፋ በሰው ልጆች ጤና፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በአካባቢ ላይ ከፍተኛ አደጋ በመደቀን የዜጎችን በንጹህና ደህንነቱ በተጠበቀ አካባቢ የመኖርን ሕገ መንግስታዊ መብትን (የኢፌድሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 44 እና 93 ይመልከቱ) ጭምር የሚጋፋ በመሆኑ ምርቱና ስርጭቱ እንዲቋረጥና ክልከላ እንዲደረግ እርምጃ እንዲወሰድ መንግሥታችንን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ለጥያቄያችን ምክንያቶቹ የሚከተሉት ናቸው፣
መግቢያ
ፕላስቲኮች ከነዳጅ የተመረቱ ሰው ሠራሽ ንጥረ ነገሮች ሲሆኑ፣ አይበሰብሱም፣ ይሰባበራሉ፣ በኋላም ወደ ማይክሮፕላስቲክነት ይቀየራሉ። እነዚህ በአየር፣ በውሃ፣ በአፈርና በምግብ ሰንሰለት ይሰርጋሉ። የቆሻሻ አስተዳደር ውስን በሆነባት በኢትዮጵያ ይህ አደጋ በፍጥነት ይጨምራል።
በሰው ጤና ላይ ተፅዕኖ
ፕላስቲኮች እንደ ፍታሌትስ, BPA, ከባድ ብረቶች እና POPs ያሉ አደገኛ ኬሚካሎችን ይይዛሉ። እነዚህ ከሆርሞን መዛባት፣ የእድገት ችግሮች፣ የመተንፈሻ በሽታዎችና የካንሰር አደጋ ጋር የተያያዙ ናቸው። ለወለል ቀርበው ስለሚጫወቱ እና አዘውትረው እጃቸውን ወደ አፋቸው የማስገባት ባህሪ ስላላቸው ሕፃናት በተለይ ለዚህ አደጋ ይጋለጣሉ።
ፕላስቲክ ቄጠማ ፣ የተለየ አደጋ
ፕላስቲክ ቄጠማ በቤት ውስጥ በበዓላት ይጎዘጎዛል። መረጋገጥና መጠረግ ሲደጋገም የማይክሮፕላስቲክ ትንንሽ ፋይበሮች እየረገፉ በመተንፈሻ አካላት ውስጥ ይገባሉ። ብዙውን ጊዜ የፕላስቲክ ቄጠማ መጨረሻው መቃጠል ነው፤ መቃጠሉ ዳዮክሲን እና ፊዩራን የተባሉ እጅግ መርዛማ በካዮችን በጭስ መልክ ይለቃል።
በእንስሳትና በግብርና ላይ
እንስሳት ፕላስቲክን እንደ ምግብ ሊበሉት ይችላሉ፤ በመሆኑም የምግብ ቧንቧ መዝጋት፣ የምግብ መውሰድ መቀነስ፣ ሞት ያስከትልባቸዋል። አፈር ይበከላል፤ የማይክሮብ እንቅስቃሴ ያሽቆለቁላል፣ ምርታማነት ይቀንሳል።
በአካባቢና በውሃ ስርዓት
የውሃ መፍሰሻ ቦዮች መዘጋት፣ ጎርፍ፣ የወንዞች ብክለት ይጨምራል። ማይክሮፕላስቲኮች በዓሦች ይበሉና፣ ወደ ሰው ልጅ የምግብ ዑደት ተመልሰው በመግባት ሰውን ይጎዳሉ።
ከአገራዊ አቋም ጋር ግጭት
ፕላስቲክ ቄጠማ ምርትና ሰርጭት የ “ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ (CRGE)” ራዕይን ያኮስሳል፣ የቤት ውስጥ ኢኮኖሚን ያዳክማል፤ ተፈጥሯዊ ቄጠማን ይተካል፣ የውጭ ምንዛሬ ያባክናል፣ ልንከላከለው የሚገባን ብክለትን ያስገባል።
መደምደሚያ
በኢትዮጵያ አውድ፣ ፕላስቲክ ቄጠማ ከፍተኛ የህዝብ ጤናና የአካባቢ አደጋ ነው። መከልከሉ በሳይንስ ላይ የተመሰረተ፣ ከባህል ጋር የተጣጣመ፣ በኢኮኖሚ የሚያዋጣ እና አስፈላጊ ውሳኔ ነው።
ስለዚህ፣ መንግሥትን የምንጠይቀው፣
- ፕላስቲክ ቄጠማን ማምረትንም ሆነ ወደ ኢትዮጵያ ማስመጣትን በአስቸኳይ እንዲከልክል፤
- ፕላስቲክ ቄጠማን ከገበያ እና ከህዝብ አጠቃቀም እንዲያስወግድና ተግባራዊ ክትትልና ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ፤
- ተፈጥሯዊ አማራጮችን እንዲያበረታታና እንዲደግፍ፣ ይህም የገጠር ህይወትን እና የአካባቢ የእሴት ሰንሰለቶችን ያጠናክራልና፤
- ስለ ፕላስቲክ ቄጠማ የጤና፣ የአካባቢና የኢኮኖሚ ተፅዕኖ የህዝብ ግንዛቤ እንዲካሄድ ድጋፍ እንዲያደርግ፤
በመሆኑም፣
እኛ ከዚህ በታች ስማችን የተዘረዘረ፣ የህዝብ ጤናን ለመጠበቅ፣ የእንስሳትን ህይወት ለማክበር፣ አካባቢያችንን ለማስጠበቅ እና እውነተኛ አረንጓዴና ሃገር በቀል ኢኮኖሚ ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆናችንን እናረጋግጣለን። ፕላስቲክ ቄጠማን መከልከል አስፈላጊ፣ ተግባራዊ እና አሁን የሚያስፈልግ እርምጃ መሆኑንም እናምናለን።
ሕይወትን እንምረጥ፣ ባህላችንን እናከብር፣ ወደፊት እንመልከት!
ፈራሚዎች፦
- ፍሬው ከፍያለው - firewkef@gmail.com
- ዶ/ር ፋሲካ በላይ - fasik.belay@gmail.com
- ዶ/ር ይታያል አዲስ - yituaddis@gmail.com
- ዶ/ር መሠረት ሃብታሙ - mesihabenv@gmail.com
- ኤፍራታ አለማየሁ - ephratus12@gmail.com

Victory
Share this petition
Share this petition
Petition created on 16 January 2026