የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሒደት አካታች እና ግልጽ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ

The Issue
ኢትዮጵያ “ለዘመናት ሲንከባሉ የመጡ ውስጣዊ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት የሚያስችሉ የፖለቲካ ባሕል ለማዳበር እና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ምቹ መደላድል መፍጠር”፣ “በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል እንዲሁም በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል፣ መተማመን የሰፈነበትና አዲስ የፖለቲካ ስርዓት መፍጠር”፣ “ወቅታዊ ችግሮች ዘላቂ በሆነ መንገድ ተፈተው አስተማማኝ ሰላም የሚረጋገጥበትን የፖለቲካ እና የማኅበራዊ መደላደል ማመቻቸት”፣ “ሀገራዊ መግባባት እና ጠንካራ ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት በመገንባት ጽኑ መሠረት መጣል”[1] የሚሉ እና ሌሎችም ዓላማዎችን ያነገበ የሀገራዊ ምክክር ሒደት በ2014 ጀምራለች። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የተመሠረተበት የሕግ ማዕቀፍና ተቋማዊ አደረጃጀት ተፈጥሮ ወደ ሥራ ተገብቷል።
በ2014 የወጣው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 “በአገሪቱ የሐሳብ መሪዎች እንዲሁም የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል” ለረዥም ጊዜ ሲንከባለሉ የቆዩ ልዩነቶች መኖራቸውን በመጥቀስ፣ “እጅግ መሠረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አካታች አገራዊ ምክክሮችን ማካሔድ የተሻለ ሀገራዊ መግባባትን መገንባት”[2] አስፈላጊ መሆኑን ይገልጻል። አዋጁ እነዚህን “እጅግ መሠረታዊ፣ ሀገራዊ፣ አለመግባባቶች”ን በዘላቂነት ለመፍታት “አካታች” እና ተአማኒ ሒደት በመከተል “ሀገራዊ መግባባትና መተማመንን” መፍጠር እንደሚያስፈልግ አበክሮ ይገልጻል።
እኛም ይህንን ትልቅ እና ወሳኝ ዓላማ ለማሳካት ኮሚሽኑ እስካሁን የተጫወተውን ሚና እናደንቃለን፣ ኢትዮጵያውያን ያለንበት የግጭት ዐውድ የኮሚሽኑን ሥራ ከፍተኛ ተግዳሮት እንደደቀነበትም እንረዳለን። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የሐሳብ ልዩነት ያላቸው አካላትን አካታችነትን እና የአካሔድ ግልጽነትን በተመለከተ ብዙ ቅሬታዎች እየተነሱ ይገኛሉ። የግልጽነትና የአካታችነት ጥያቄዎች በትግበራ ላይ ለሚገኘው ሀገራዊ ምክክር መሳካት ወይም መውደቅ የማይተካ ሚና እንዳላቸውም እናምናለን። የዚህ ግልጽ ጥሪ ዋና ዓላማም ኮሚሽኑ በምክክሩ ሒደት የተሻለ ግልጽነትን እንዲሁም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አካታች እንዲሆን የሚያስችሉ ተጨማሪ ጥረቶች እንዲደረጉ ለማሳሰብ ነው።
አዋጁ 11 የአገራዊ ምክክር መርሖዎችን የሚዘረዝር ሲሆን አካታችነት፣ ግልጽነት፣ እና ተዓማኒነት ቀዳሚዎቹ መርሖዎች ሆነው ተዘርዝረዋል። በመሆኑም አስከትለን የምንዘረዝራቸው የአካታችነትና የግልጽነት ቅሬታዎች ሳይፈቱ ቀጣይ ዝግጅቶችን እና ዋናውን የምክክር መድረክ ማዘጋጀት ሀገራዊ ምክክሩ የሚያስከትላቸው ለውጦች የብዙኃን ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ሊያደርግ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አለን።
- ቅድመ መቋቋም ጉድለቶች፦ የሀገራዊ ምክክሩን ኮሚሽን የሚያቋቁመው አዋጅ አወጣጥ ሒደት ጀምሮ ተቋማዊ አደረጃጀቱን የሚመለከቱ ቅሬታዎች ከእነዚህ የአዋጁ መርሖዎች አንፃር የቀረቡ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች አሉ። የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ሲወጣ በሁሉም የባለድርሻ አካላት በቂ ምክክር አልተደረገበትም።[3] ኮሚሽኑን የሚመሩ ኮሚሽነሮችን ለመምረጥ ሕዝባዊ ጥቆማዎች የቀረቡ ቢሆንም፥ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፋ ከተደረጉ የመጨረሻ ዕጩዎች የተለዩበት መርሕ ግልጽነት የጎደለው ከመሆኑም ባሻገር፣ የመጨረሻዎቹ እጩዎች መካከል ያልነበሩ ግለሰቦች በኮሚሽነርነት መመደባቸውም ሒደቱ ወጥ የሆነ አሠራር የሌለውና ግልጽ የእጩዎች መረጣ መሥፈርቶች አለመኖሩን ያሳዩ አጋጣሚዎች ነበሩ።[4] ይህም የተወሰኑ ባለድርሻ አካላትን በሒደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲሸረሸር አድርጓል፤ በውጤቱም በግልጽ ስጋታቸውን በማንሳት ከምክክር ሒደቱ ገና ከጅምሩ ራሳቸውን ያገለሉ ባለድርሻ አካላት መኖራቸው ይታወቃል[5]። እነዚህ ችግሮች ኮሚሽኑ በቅድመ መቋቋም ላይ ሳለ ተፈጥረው የወረሳቸው ቢሆኑም በግልጽነት መርሕ ሁኔታውን ለማጥራት ወይም ከባለድርሻ አካላት ጋር መተማመን ያልፈጠረበት ችግር ነው።
- ከግጭቶች እና የግጭት ተዋናዮች ተሳትፎ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች፦ አንዱ የኮሚሽኑ ዓላማ “ወቅታዊ ችግሮች ዘላቂ በሆነ መንገድ ተፈተው አስተማማኝ ሰላም የሚረጋገጥበትን የፖለቲካ እና የማኅበራዊ መደላደል ማመቻቸት”[6] እንደመሆኑ እና በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ሌሎችም ክልሎች ፖለቲካዊ መሠረት ያላቸው ግጭቶች እየተካሔዱ በመሆኑ፣ ኮሚሽኑ በተቋቋመለት ዓላማ መሠረት፣ ታጣቂ ቡድኖቹ በሰላማዊ መንገድ የሀገራዊ ምክክሩ ላይ ለማካተት ከሚዲያ ቃለ ምልልሶችና ጥሪዎች የተሻገረ፣በይፋ የተነደፈ ዕቅድ አለመኖሩ፣ ካለም ለዜጎች ግልጽ አለመደረጉ ምክክሩ አንድ ግቡን እንዳይመታ ያደርገዋል የሚል ስጋት አሳድሮብናል። ኮሚሽኑም ይኼንን ትልቅ ተግዳሮት እንደሚገነዘበው እና መፍትሔ እንደሚሻው ገልጾ የነበረ ሲሆን ችግሩን በመቅረፍ እና አጥቃላይ ሒደቱን ውጤታማ እንዲያደርግ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
- ምክክሩን ከተለያዩ አካላት ተፅዕኖ ነጻ ማድረን በተመለከተ፦ የሀገራዊ ምክክር ሒደቱ ከመንግሥት ተፅዕኖ ራሱን የሚከልልበት አሠራር ባለመዘርጋቱ ወይም የዘረጋውን አሠራር ለባለድርሻ አካላት ግልጽ ባለማድረጉ፣ እንዲሁም በተሳታፊዎችና በምክክር አጀንዳ መረጣ ሒደት ላይ አንድ ወገን ወይንም በተለያዩ መንገዶች የተደራጁ አካላት በተለያየ መልክና የአጀንዳ ቅርፅ የምክክር ሒደቱን እንዳይቆጣጠሩ ለማድረግ እንዲቻል የተቀመጠ ይፋ አሠራር ባለመኖሩ፣ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ምክንያቶች ያሉባቸውን ችግሮች መለየትና አጀንዳ ማስያዝ የሚችሉበት በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የአቅም ግንባታ ሥራ ባለመሠራቱ፥ እንዲሁም ኅዳጣን አጀንዳ ከማቅረብ ባለፈ በብዙኃኑ የማይዋጡበትን አሠራር ባለመዘርጋቱና በግልጽ ባለመታወቁ፥ ብሎም ሒደቱን ግልጽ፣ አካታችና ተዓማኒ ለማድረግና ለመከታተልና ለመመዘን የሚረዱ ዝርዝርና በግልጽ የተቀመጡ አሠራሮች ባለመኖራቸው የምክከር ሒደቱ ከጅምሩ አንስቶ ሲከተሉት የመጡ መሠረታዊ የተዓማኒነት፣ የአካታችነትና የግልጽነት ጥያቄዎች እስከመጨረሻው አብረውት እየተጓዙ በመሆኑ ምላሽ ይፈልጋሉ።
- በምክክሩ እንድንሳተፍ አልተደረንም የሚሉ አካላት ቅሬታ፦ ኮሚሽኑ አካታችነትን ለማረጋገጥ ይረዳሉ ያላቸውን መመሪያዎችና ሒደቶች ያስተዋወቀ ቢሆንም፥ በአዲስ አበባ በተደረገው የአገራዊ የምክክር የአጀንዳ መረጣ ሒደት ላይ የታዩ ክፍተቶች ቃል በተገባው ልክ አካታችነትንና ግልጽነትን ወደ መሬት የማውረድ ሥራው ምን ያህል አዳጋች እንደሆነ አሳይቷል። ከዚህ ባለፈም የሀገራዊ የምክክር ሒደቱ፣ በተለይም የተሳታፊዎች ምርጫ መስፈርቶችን በተመለከተ የግልጽነትና አካታችነት ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረ ሲሆን፥ ለአብነትም የአገሪቱ ሦስት የእምነት ተቋማት፥ ማለትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን[7] እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት[8] በተለያዩ ጊዜያት በሀገራዊ የምክክር ሒደቱ ላይ የአካታችነት እና የዉክልና ጥያቄ አንሥተዋል። እነዚህ ቅሬታዎች የሒደቱን አካታችንት በከፍተኛ ጥያቄ ውስጥ የሚጥሉት ሆኖ አግኝተነዋል።
- የአንዳንድ አካላት ያልተመጣጠነ ተሳትፎን እና ተፅእኖን ስለመከላከል፦ ከግንቦት 21፣ 2016 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በተደረገው የሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ ማሰባሰብ የመጀሪያ መርሐ ግብር ማለትም የአዲስ አበባው የአጀንዳ ልየታ ወቅት በብዙዎቹ ቡድኖች ውስጥ የመንግሥትን አቋም የሚያንፀባርቁ ተሳታፊዎች የተመደቡባቸው ናቸው። እነዚህ ቡድኖች የወረዳ ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የመንግሥት አካላት ተወካዮች፥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተብለው የተሳተፉ ግለሰቦች እንዲሁም የአንዳንድ ማኅበራት ተወካዮች ሲሆኑ፥ የተሳታፊዎቹን ስብጥር ብሎም የአጀንዳ ምርጫውን ወደ አንድ አካል እንዳያደላ የሚያደርግ አሠራር በግልጽ አልተቀመጠለትም። በተጨማሪም፣ ሒደቱ በተለይም የመንግሥት ወይም የገዢውን ፓርቲ ተወካዮችን በተለያዩ እርከኖች እና በተጠቀሱት የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካይነት በማሳተፍ ያልተመጣጠነ ውክልና እንዲኖረው ሊያደርግ ስለሚችል፥ ይህንን ለመከላከል የሚያስችል አሠራር መኖር አለበት፤ ካለም በግልጽ ይፋ መደረግ አለበት። በተጨማሪም በመክፈቻ መድረኩ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ንግግርን ጨምሮ ሌሎች የተስተዋሉ ንግግሮች እና አቋሞች በአዲስ አበባውም ሆነ ሊደረጉ የታሰቡ ሌሎችን መድረኮች ላይ በሚደረጉ ውይይቶች እና ውሳኔዎች ላይ ተፅዕኖ የማድረግ ዕድላቸው ከፍተኛ በመሆኑ ተዓማኒነቱን ይጎዳዋል። ይህንን ለመከላከልም ግልጽ አሠራር ያስፈልጋል ብለን እናምናለን።
ኮሚሽኑ ለነዚህ እና ሌሎችም የግልጽነት፣ ተዓማኒነት እና አካታችነት ጥያቄዎች መልስ እየሰጡ እና ቅሬታዎችን እየፈቱ በመሔድ ፈንታ፣ ያለበቂ ማብራሪያና አጥጋቢ አሠራር ወደፊት መገስገሱን ቀጥሏል። በቅርብ ጊዜ ውስጥም ዋና ጐባኤውን ሊያደርግ እንደሚችል ይታመናል። ይሁን እንጂ በእነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ ያለፈው ሒደትና የምክክር ውጤት በዘላቂነት ያመጣል የተባለለትን ሰላም፣ እንዲሁም በኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል እና በመንግሥትና በኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል ያልውን ግንኙነት ለማደስ ይችላል ብለን አናምንም። ስለሆነም ኮሚሽኑ ለነዚህ ጥያቄዎቻችን አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጠን ይፋዊ ጥሪ እናደርጋለን።
ይህን ይፋዊ የግልጽነትና የአካታችነት ጥሪን ከታች ይፈርሙ።
---
ምንጮች
[1] አዋጅ ቁጥር 1265/2014 አንቀጽ 6
[2] የአዋጅ ቁጥር 1265/2014 መቅድም
[3] "ከየኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሀገራዊ ምክክር የዝግጅት ሂደትን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ" የካቲት 10፣ 2014 ፣ የፌስቡክ ልጥፍ https://www.facebook.com/EthiopianPoliticalPartiesJointCouncil/posts/244670637857247 (ሔምሌ 8፣ 2014)
[4] አዋጅ ቁጥር 1265/2014 አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 4 መሠረት "አፈ ጉባዔው ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማኅበረሰብ ዴርጅቶች፣ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አመራሮች እና ተወካዮች ጋር በቀረቡት ዕጩዎች ሊይ ምክክር ያደርጋል" የሚል ሲሆን ይኼም ሳይሆን ቀርቷል።
[5] "OFC, ONLF say Dialogue Commission process unrepresentative, not impartial; decline Parliament invitation today", Addis Standard, 4 February 2022 እንዲሁም "የኦፌኮ የብሔራዊ ምክክሩ የማሻሻያ ሀሳብ ደብዳቤ" ዶቼዌሌ አማርኛ 10 ጥር 2014
[6] አዋጅ ቁጥር 1265/2014 አንቀጽ 6/6
[7] "ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን [የሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ ማሰባሰብ ማስጀመሪያ ዕለት አተቃላይ ሒዳቱን በተመለተ] ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፣ ግንቦት 29፣ 2016
[8] “ሀገራዊ ምክክር የሕዝበ ሙስሊሙ ተሳትፎ “በቁጥሩ ልክ መሆን አለበት” ያለው መጅሊስ፤ የተሳታፊ አካላት ልየታ በድጋሚ እንዲቃኝ ጠየቀ”፣ሚንባር ቲቪ፣ ግንቦት 8፣ 2016

1

Petition Updates
Share this petition
Petition created on 23 July 2024