Make the Ethiopian Sign Language a working Language

The Issue
የኢትዮጵያ የምልክት ቋንቋ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን እንጠይቅ!
በኢትዮጵያ ምን ያህል መስማት የተሳናቸው ሰዎች እንዳሉ ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከመስማት ጋር የተገናኘ ጉዳት ያለባቸው ዜጎች በሀገራችን እንደሚኖሩ ይገመታል።
የምልክት ቋንቋዎች የራሳቸው ሰዋሰው፣ መዝገበ ቃላት እና ዘዬ ያላቸው የተሟሉ፣ ቋንቋዎች ሲሆኑ፤ ከውልደት ጀምሮ መስማት ለተሳናቸው ሕጻናት ደግሞ ብቸኛ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ነው፡፡
ከኢትዮጵያ የብሔር ብዝኃነት አንጻር ተጨማሪ ቋንቋዎችን በሥራ ቋንቋነት ለማካተት የሚያስችል የቋንቋ ፖሊሲ በቀረጻ ሂደት ላይ መሆኑ ቢታወቅም፤ መስማት ለተሳናቸው ሰዎች የግድ አስፈላጊ የሆነውን የምልክት ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ለማድረግ በቂ ትኩረት አላገኘም።
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነትን በአዋጅ ቁጥር 676/2002 አጽድቃ ተቀብላለች። በዚህም የምልክት ቋንቋ ትምህርትን የማመቻቸትና የማበረታታት ግዴታ አለባት።
የምልክት ቋንቋን ይፋዊ የሥራ ቋንቋ ማድረግ መስማት የተሳናቸውን ሰዎች መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ፣ በማኅበረሰብ ውስጥ በሁሉም ዘርፍ የሚኖራቸውን የተሳትፎ መጠንና የአገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ ብሎም ሰብአዊ መብቶቻቸው ሙሉና ውጤታማ በሆነ ደረጃ እንዲረጋገጡ ለማስቻል አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡
ይህ የፊርማ ሥነሥርዓትም ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀና ለጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተጻፈ ደብዳቤ ላይ ዜጎች ድምጽ እንዲሆኑ ለመጠየቅ ያለመ ነው።
ሙሉ ደብዳቤውን ከታች ካለው ምስል ወይም ሊንኩን በመጫን ያገኛሉ
� https://t.ly/Iq7j
638

Petition Updates
Share this petition
Petition created on April 7, 2023