

በፋሺስታዊው የኦሮሙማ ቡድን በነገደ አማራ ሕዝብ ላይ በታወጀው ወታደራዊ ኢኮኖሚያዊና መረጃዊ ጦርነት የአማራን ድምጽ ለመዝጋት የተወሰዱ የእፈና እርምጃዎች
ውድ ወገኖች፣ ውድ እድምተኞችና ውድ አንባቢያን በሙሉ፣
በያላችሁበት ሁሉ ሰላማችሁ የተጠበቀ ይሁን እያልኩ ወደዛሬው አርእስት ሳመራ የአማራን ሕዝብ ድምጽ ለማፈን በተወሰዱ ሕገ ወጥ የአፈና እርምጃ ከተዘጉት ሚዲያዎች ውስጥ የሶስቱን ሚዲያዎችን ታሪክና ለምንና እንዴት ኢላማ እንደተደረጉ በመግለጽ በመደምደሚያዬ ላይ ይህንን ጥቃት ከመከላከልና ብሎም ከማስቀረትም አንጻር የዚህን ፔቲሽን ሚናን በመጠቆም እቌጫለሁ - ውድ ግዜያችሁን ሰውታችሁ በዚህ ዘመቻ ላይ በመሳተፍ ፔቲሽኑን በፊርማ፣በማሰራጨት፣ ስርጭቱ እንዲሰፋና እንዲጨምር ደግሞ በገንዘብ አስተዋጾኦ ላደረጋችሁና እያደረጋችሁ ላላችሁ ውድ ወገኖች በሙሉ የከበረ ልባዊ ምስጋናዬን እየገለጽኩ አሁንም ፔትሺኑ የተከፈተበትን ዓላማ ግብ ይመታ ዘንድ የእናንተ አስተዋጾኦና ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ መሆኑን በመግለጽ ተሳትፎእችሁን አጠንክራችሁ እንድትቀጥሉ በድጋሚና በታላቅ አክብሮት አደራ እላለሁ።
ውድ ወገኖች
ለምንድነው ስርዓቱ የአማራን ድምጾች ማፈን የፈለገው ?? በተለይም ተመርጠው ከተዘጉት በርካታ ሚዲያዎች ውስጥ ይህ ፔቲሽን ለምን እና እንዴት አድርጎ ነው የሶስት ሚዲያዎችን - ኢትዮ360 ሚዲያ ፣ የጋዜጠኛ አበበ በለው አዲስ ድምጽና የባሮን ቲውብ ቻናል መርጦ ለማቅረብ የበቃው የሚሉትን ጥያቄዎች የሚመልስ ምጥን ዘገባን በማስቀደም ልጀምር፣
♦️ የአማራን ድምጽ ለማፈን ለምን አስፈለገ?? እንዴትስ ተቻለ??
ማንኛውም አፈና ተግባራዊ ሆኖ ተፈጻሚ የሚሆነው የእንድ አፋኝ ቡድን፣ ኋይል ድምጹ እንዳይሰማ ማፈን አለብኝ ብሎ በሚወስደው የአፈና እርምጃ ምክንያት ብቻ የሚከሰት ክስተት ሳይሆን የታፋኙ ወገን አፈናውን ተቀብሎ ዝም የማለት ትብብር ሲታከልበት ብቻ ነው የአንድ አፈናን እርምጃ ውጤታማነትን መግለጽ የሚቻለው።
ታዋቂው ጥቁር አሜሪካዊ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የነበረው ማልኮልም ኤክስ በዚህ ዩንቨርስ ውስጥ ትንኝ የምታክል ፍጥረትን እንኴን መጫንና ማፈን ስትጀምር ታምጽብሃለች በማለት አፈና ስኬታማ የሚሆነው በታፋኙ ወገን ዝምታ ተባባሪነት እንደሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ ቀደም ብሎ ተናግሯል።
አዎን - የአማራን ድምጾች የማፈን «መንግስታዊ» በሆነ ዘመቻ ሕገ ወጥ የሆነ እርምጃ በርካታ የአማራ ሚዲያዎች በመታገዳቸው የተነሳ - እነሆ ይህንን የእፈናን እርምጃ በመቃወምና አፈናውንም ለማስቆም በሚል ይህ እናንተን ውድ ተሳታፊዎችን አቅፎ በማሳተፍ አንታፈንም ብሎ በመነሳት ይህንን ፔትሺን መክፈት የተቻለውና - የስርዓቱ የአፈና ተግባር ተከትሎ የአጸፌታን እርምጃ እንዲፈጠር ችሏል።
የአማራን ድምጽ ለማፈን የተፈለገበትና ብሎም የተቻለበት ምክንያት፦
� 1ኛ - የነገደ አማራን ሕዝብ ከተቀረው ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰብ ውስጥ በማንነቱ ብቻ ለይቶና ነጥሎ እኔ ላሳካ ለተነሳሁለት የሁሉንም ኬኛ የኦሮሙማ ዓላማና ግብ ተገዳዳሪ እንቅፋት የሚሆነኝ የአማራ ሕዝብ ነው ብሎ በማመን መንግስታዊ ጦርነት በመክፈቱ
� 2ኛ - ለዓላማዬ መሳካት መጥፋት ያለበትን ጠላቴን ማጥፋት አለብኝ ብሎ ጦርነት ሲከፍት- ጦርነቱ በኢኮኖሚ፣በፖለቲካ፣በወታደራዊ ኋይልና በመረጃ መስክ የተከፈተ በመሆኑ የአማራን ድምጽ የማፈኑ እርምጃ የጦርነቱ አንዱ አካል ሆኖ እናያለን።
ለዚህ ዘመቻው ደግሞ ፋሺስታዊው ስርዓት ልክ ወታደራዊውን ዘመቻ የሚመራበትን የጸጥታ ግብረ ኋይል የሚባል ስብስብ ፈጥሮ ጦርነቱን እንደሚመራ ሁሉ የመረጃ፣ የፕሮፖጋንዳውንና የሚዲያውን ክፍል የሚያዝበትንም ልዩ ግብረ ኋይል አቌቁሞ 7/24 ሰዓት የማሕበራዊ ትሥስር ገጾች፣በሳተላይት የሚተላለፉ ቴሌቪዥን ሚዲያዎች በዩቲውብና መሰል ማሕበራዊ ትሥስር የሚተላለፉትንና በአጭር ሞገድ ፍሪኩዌንሲ የሚሰራጩ ራዲዮ ጣቢያዎችን እየተከታተለ የማፈን እና የማዘጋትን ስራ በመስራት ላይ ይገኛል።
ይህ የመረጃ የፕሮፖጋንዳና የሚዲያው ግብረ ኋይል በራሱ በአቢይ አህመድ በቀጥታ የሚታዘዝ ቢሮውንም በጠ/ም ጽ/ቤት አድርጎ ከኢንሳ( INSA) እና ከመላው ሀገር በተውጣጡ አይ ቲ ( IT) ባለሙያዎች የሚገኙበትና እጅግ ከፍተኛ በሆነ የውጭ ምንዛሪ ክፍያ ከቻይና እና ከእስራኤል - ማለትም - በየሀገራቱ መንግስታት እውቅና እና ምደባ ሳይሆን ግለሰቦቹ በግላቸው ተመልምለው በመጡ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ታግዞ ስራውን እየሰራ ያለ ቡድን ሲሆን የግብረ ኋይሉ የበላይ ተጠሪ ሆኖ ከአቢይ ጋር በቀጥታ እየተገናኝ ትእዛዝ የሚቀበለውና የተሰራውንም ስራ ሪፖርት በማድረግ ደረጃ የተቀመጠው የአቢይ አህመድ የቅርብ ጋደኛ ወዳጅና ተጠቃሚ የሆነው በቅጽል ስሙ ሶል ቴክ ( ሰለሞን ካሳ) የሚመራ ግብረ ኋይል ነው ይህንን የአፈናን ስራ እየሰራ ያለው።
ይህ ግብረ ኋይል - ወታደራዊው ኋይል የደህንነት የመረጃውና የፖለቲካው ኋይል በመላው የአማራ ሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ የጭፍጨፋ ዘመቻን ከፍቶ በሚያጧጡፍበት ሁኔታ ይህ የመረጃ የፕሮፖጋንዳና የሚዲያው ግብረ ኋይል ደግሞ በማሕበራዊ ትሥስር ገጾች ላይ በትንሹ ከአምስት ሺህ በላይ ተከታይ ያላቸውና የስርዓቱን ወንጀሎችን በመግለጽ የሚተጉ ጋዜጠኞችን፣ አንቂዎችን፣ ፖለቲከኞችንና ጸሓፊዎችን ኢላማው አድርጎ ይዘምትባቸዋል። ተደራሽነታቸውና ስርጭታቸው ሰፊ የሆኑ ሚዲያዎችን ለይቶና መርጦ የማዘገትን ዘመቻ በመክፈት 7/24 ሰዓት በመስራት ላይ ይገኛል።
♦️ ለአፈና የተመረጡት ሚዲያዎች ማንነትና ለመታፈን ያበቃቸው ተግባር፦
በዚህ ግብረ ኋይል ዘመቻ ከአየር ላይ የወረዱ ሚዲያዎች በደርዘን ይቆጠራሉ። ሆኖም በስርጭታቸው ሽፋን እና በሚያሰራጩት መረጃ ጥራት በመላው የኢትዮጲያ ሕዝብ ዘንድ በመረጃ ሳተላይት ቴሌቪዥን እየተላለፉ ከታፈኑት ውስጥ እጅግ ወሳኝና ግንባር ቀደም የሆኑትን ሁለቱን ሚዲያዎች - ኢትዮ 360 ሚዲያና የጋዜጠኛ አበበ በለው አዲስ ድምጽ ራዲዮና ቴሌቪዥን በተለየ ሁኔታ ተለይተውና ተመርጠው በዚህ ግብረ ኋይል የተዘጉ ሲሆን የስርጭት ሽፋኑን በመረጃ ሳተላይት ቴሌቪዥን ሳያደርግና በዩቲውብ ቻናል ብቻ በማስተላለፍ ከፍተኛ ተከታይ ማፍራት የቻለውንና በግብረ ኋይሉ ሰለባ የሆነውን ባሮ ቲውብ በማካተት በሶስቱ ሚዲያዎች ላይ ይህንን የፔቲሽንን ዘመቻ ለመክፈት የቻልነው።
♦️ ሶስቱ ሚዲያዎች የተዘጉበት ምክንያት፦
� 1ኛ - ኢትዮ-360 ሚዲያ
(https://m.youtube.com/watch?v=ItteKGWSX-M&t=433s
https://www.ethio360media.com/ )
ከጋዜጠኛ ኢየሩሳሌ ተክለጻዲቅ በደረሰኝ መረጃ መሰራት ከላይ የምታዩት ኢትዮ360 ቻናል ስቱዲዮ 4 ለአስራ ሁለተኛ ግዜ ያህል የተከፈተ አዲስ ቻናል ነው። ይህ 12 ግዜ የመዘጋት እርምጃ በተቌሙ ላይ የተወሰደው በሚደንቅ ሁኔታ ሁለት ወር እንኴን ባልሞላ አጭር ግዜ ውስጥ ነው።
ኢትዮ 360 ሚዲያ ከሀምሌ 2019 ጀምሮ ለአየር በመብቃት በቅርብ ግዜ የኢትዮጲያ ታሪክ ውስጥ ምትክ የለሽ ስራን በመስራት አሻራውን ያኖረ ታላቅ የህዝብ ድምጽ ሲሆን ከወራት በፊት በተዘጋበት ወቅት ከአራት ሺህ በላይ ስራዎቹን በቪዲዮ ለሕዝብ ያበቃና ከ597,000 በላይ ሰብስክራይበሮችን ማፍራት የቻለ እጅግ ታዳጊ ሚዲያ ተቌም ነው - ኢትዮ 360 ሚዲያ ማለት።
ኢትዮ 360 ሚዲያ ማለት በአጭሩ በማንም ሌላ ሚዲያ የማይተላለፉ የኦሮሙማው ስርዓት ገበናዎችና እጅግ ጥብቅ ምስጢሮች የሚተላለፉበት ሚዲያ ከመሆኑም በላይ ከታች ሞያሌ እስከ መቀሌ ከምእራብ ጋምቤላ እስከ ምስራቁ ደዋሌ የጠረፍ ከተማ በመላው የኢትዮጲያ ግዛት ውስጥ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ዘንድ ዘወትር ምሽት በጉጉት የሚጠበቅ ድንቅ መረጃ አቅራቢ ሚዲያ ተቌም ለመሆን የበቃ ነው።
ኢትዮ 360 ሚዲያ በፋሺስታዊው የኦሮሙማ ስርዓት ጥርስ ውስጥ ያስገባው እማይገኙ የስርዓቱ ውስጠ ገበና ምስጢር እያወጣ ለጸሓይ የማስጣቱ ስራ አቢይ አህመድ አሊን ምንሊክ ቤተመንግስት ውስጥ ኢትዮ360 አለ ብሎ እንዲያምንና ሁሉንም ምኒስትሮች እንዳያምን ያደረገን መረጃን በማግኘትና ብሎም በማቅረብ ለስርዓቱ የጉሮሮ ውስጥ አጥንት ለመላው የኢትዮጲያ ሕዝብ ደግሞ እውነተኛ መረጃን አቅራቢ ሚዲያ በነጠፈበት ሀገር እውነተኛ መረጃን የሚያደምጡበት ምርጥ አማራጭ በመሆን በናፍቆት የሚጠበቅ ሚዲያ ለመሆን የቻለ ነው።
በአቢይ አህመድ የሚመራው ፋሺስታዊው የኦህዴድ/ብዓዴን ብልጽግና ቡድን መራሹ የመረጃ፣ፕሮፖጋንዳና የሚዲያ ግብረ ኋይል ቁጥር -1- ጠላት ተደርጎ ኢላማ ውስጥ የተደረገው ኢትዮ360 ሚዲያ በመላው ኢትዮጲያ በሚሰራጨው የመረጃ ሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት በእያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ቤት ውስጥ እውነተኛን መረጃ ይዞ የሚደመጥ የመሆኑ ጉዳይ ቀዳሚ ኢላማ እንዲሆን አድርጎታል።
አቢይ አህመድ የ360 መረጃ ምንጮች ማንጠፍና ማድረቅ የሚቻለው መረጃቸውን ተቀባይ የሆነውን ሚዲያ በመዝጋት ነው በሚል ስትራቴጂ መጠነ ሰፊ ገንዘብ የሰው ኋይልና የቴክኖሎጂ አቅርቦት በመደበለት ግብረኋይል ቡድን ቁጥር -1- ኢላማ ተደርጎ ሊዘመተበት የበቃ ሚዲያ ነው። በዚህም ምክንያት እጅግ በሚደንቅ ሁኔታ እጅግ አጭር በሆነ ግዜ ውስጥ ብቻ 12 ግዜ ያህል የተዘጋና አሁናም በመንፈስ ብርቱ ጋዜጠኞቹ እንቢ አንታፈንም ባይነትና በእናንተ ውድ አድማጭ ተከታዮች እንቢታ በየእለቱ እየተዘጋ በመከፈት ለፋሺስቱ ስርዓት የጉሮሮ ውስጥ አጥንት ለሀገራችንና ለሕዝባችን ደግሞ አማራጭ ድምጽ መሆንን የቀጠለ ተቌም ሲሆን የዚህ ፔቲሽን አንዱና ብቸኛ ዓላማና ጎል ይህንን አፈና የማስቀረትን ስራ መስራት ነው።
� 2ኛ - በጋዜጠኛ አበበ በለው የሚመራው አዲስ ድምጽ ራዲዮና ቴሌቪዥን ፦
( https://addisdimts.com/main.html
https://www.youtube.com/@Abebebelew-dy7vk/about )
በጋዜጠኛ አበበ በለው ተመስርቶ እየተላለፈ ያለው አዲስ ድምጽ ራዲዮና ቴሌቪዥን ሚዲያ ዛሬ በአገልግሎት ላይ ካሉት የሀገር ውስጥም ይሁን የውጭ የግል ነጻ ሚዲያዎች ውስጥ ለድፍን ሶስት አስርተ ዓመታት በመስራት በአንጋፋነቱ ብቸኛው ሚዲያ ነው።
አዲስ ድምጽ ራዲዮና ቴሌቪዥን በመረጃ ሳተላይት ቴሌቪዥን በመላው ኢትዮጱያ የሚደመጥ ሚዲያ ሲሆን ከሳምንታት በፊት ሲዘጋ ከ170 000 በላይ ሰብስክራይበሮችን ማፍራት የቻለና ከስድስት ሺህ በላይ ቪዲዮዎችን ለእይታ ያቀረበ የህዝባችን ድምጽ ሚዲያ ነው።
ጋዜጠኛ አበበ በለው እንደ አቻ ባልደረቦቹ የኢትዮ 360 ሚዲያዎች ያልተሰሙ የስርዓቱን ውስጠ ገበና እና ድብቅ ምስጢራዊ መረጃዎችን አግኝቶ መልሶ ለሕዝብ በማቅረብ ፕሮግራሙ በጣም የመታወቁ ሁኔታ በጸረ አማራው ፋሺስታዊው የኦሮሙማው ቡድን በ2ኛ ደረጃ ኢላማ ተደርጎ ኢትዮ 360 ሚዲያ ከታገደ ሳምንታት በኋላ ለመታገድ የቻለ የአማራ ሕዝብ ድምጽ ሚዲያ ነው።
የጋዜጠኛ አበበ በለው የየእለቱ ከጎንደር እስከ ሸዋ ከጎጃም እስከ ወሎ አዲስ አበባ ያሉትን እለታዊ ፍልሚያዎችን በቀጥታ ከስፍራው የመዘገብ ፕሮግራሙ ለአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ታላቅ ግብዓት አገልግሎትነቱ እንደ እንቁ የመፈለጉን ያሕል በፋሺስቱ ጸረ አማራ ቡድን ዘንድ ግን የመንግስታችን አደጋ ተብሎ ኢላማ ውስጥ እንዲገባ ያስደረገውን ድንቅ ዘገባዎችን አቅራቢ ሙዲያ ነው።
አዲስ ድምጽን እና 360 ሚዲያን በጣም የሚያመሳስላቸው ሁኔታ፦
� ሁለቱን በመረጃ ሳተላይት ቴሌቪዥን ዘወትር ምሽት በመላው ኢትዮጲያ ግዛት ውስጥ በእያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ቤት የሚደመጡ መሆናቸው
� ሁለቱም ሚዲያ ተቌማት በአራት ኪሎ ቤተመንግስትና በባሕርዳሩ ቤተመንግስት የተወሩ፣የተፈጸሙ፣ የታሰቡ፣ የታቀዱና የሚፈጸሙ ክስተቶችን ቀድመው በማግኘት የማጋለጥ ስራን በትጋት የሚሰሩ መሆናቸው
� የአማራን ሕዝብ ትግል እራሳቸውን ሰጥተው ለእያንዳንዱ ታጋይ ድምጽ መድረክ በመሆን ከስፍራው የሚያስተጋቡ ሚዲያዎች የመሆናቸው ጉዳይ እና በመጨረሻም
� የፋሺስታዊው ኦሮሙማ የኦህዴድ/ብዓዳን እኩል ኢላማ በመሆን ተመሳሳይ ያደርጋቸዋል።
♦️ 3ኛ - ባሮ ቲውብ ቻናል
(https://youtu.be/pmpFS9qg7pk )
ባሮ ቲውብ ቻናል ከሰኔ 2018 ጀምሮ አገልግሎቱን መስጠት የጀመረ ሚዲያ ተቌም ሲሆን ሚዲያው በተዘጋበት እለት ከ163,000 በላይ ሰብስክራይበሮችን በማፍራት ከዘጠኝ ሺህ (9,000)በላይ ቪዲዮችን ለይታ ያበቃ ሚዲያ ነው።
ባሮ ቲውብ ቻናል ከኢትዮ 360 ሚዲያ እና ከጋዜጠኛ አበበ በለው አዲስ ድምጽ ራዲዮና ቴሌቪዥን የተለየ የሚያደርገው እንደ ሁለቱ ግዙፍ ሚዲያዎች ስራዎቹ በመረጃ ሳተላይት ቴሌቪዥን የማይተላለፍ ሚዲያ የመሆኑ ጉዳይ ነው።
አዎን ባሮ ቲውብ ቻናል እንደ ኢትዮ 360 ሚዲያና እንደ አዲስ ድም በመረጃ ሳተላይት ቴሌቪዥን የሚተላለፍ ባይሆንም በፋሺስታዊው የኦሮሙማው ጸረ አማራ ቡድን ጥቃት ኢላማ ከመሆን ግን አላመለጠም።
ምክንያቱም፦
ባሮ ቲውብ ቻናል በመረጃ ሳተላይት ቴሌቪዥን ባይተላለፍም በየሰዓቱ ዜናዎችን ትንታኔዎችን በማቅረብ በቀን በትንሹ እስከ አስር ስራዎችን ለአድማጭ ተመልካች ማቅረብ የቻለ ሚዲያ ከመሆኑም በላይ እጅግ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰትን መሳብና ከመቶ ሚሊዮን በላይ ደቂቃዎች መታየትን የቻለ ስራዎችን በማቅረብ ይታወቃል።
ባሮ ቲውብ ቻናል ከሚያቀርባቸው በርካታ እለታዊ የዜና የትንታኔ ዘገባዎቹ ውስጥ በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ላይ አትኩሮታቸውን ሰጥተው የሚጽፉትን ጸሓፊዎችን፣ጋዜጠኞችን፣አንቂዎችንና ፖለቲከኞችን ስራዎች - የእኔንም ጭምር ማለቴ ነው - በማቅረብ ይታወቃል።
ይህ የባሮ ቲውብ ቻናል ስርጭት ሽፋን የአማራን ድምጽ ለማፈን በተነሳው ፋሺስታዊው የኦሮሙማ ግብረ ኋይል ኢላማ ተደርጎ ለመታገድ አበቃው።
♦️ ሶስቱም ሚዲያዎች የታገዱበት መንገድ ሕገ ወጥ በሆነና የዩቲውብን ሕግና ደንብ በጣሰ መልኩ የመሆኑ ጉዳይ፦
ፋሺስታዊው የኦሮሙማው ቡድን በአማራ ሕዝብ ላይ በከፈተው ሁሉን አቀፍ የጭፍጨፋ ዘመቻ - ተመጋጋቢ በሆነ መንገድ የአማራን ሕዝብ ድምጽ ለማፈን በርካታ የአማራን ድምጽ አስተጋቢ ሚዲያዎችን ማዘጋቱንና ከእነዚህም ውስጥ የሶስቱን ዋና ሚዲያዎቻችንን መዘጋትና የተዘጉበትንም ምክንያት ከላይ ተመልክተናል።
አሁን ደግሞ ይህ ሚዲያዎቹን የማዘጋቱ ዘመቻ የተካሄደው ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ መሆኑንና ለዚህ ፔትሺን መከፈት ዋና መንስኤ የሆነውን የህጋዊነትን ክፍል ቀጥለን እንመለከታለን።
በዩቲውብ ሕግና ደንብ Community Guidelines, Rules and Regulations መሰረት ብዙዎች አንዴ ሁለቴና ሶስት ግዜ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶአቸው የመዘጋት እድል ሲገጥማቸው ማየት የተለመደ አሰራር ነው። በ Copy Right ማመልከቻዎች ቻናሎች ሁለት ግዜ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸውና በተቆረጠላቸው ግዜ ገደብ ውስጥ ተመሳሳይ ስህተት ፈጽመው የ Copy Right ማመልከቻ ከቀረበባቸው በዩቲውብ ሕግና ደንብ መሰረት ቻናሎች ይዘጋሉ።
ይህ የተለመደ የዩቲውብ የሚዱያ ቻናሎችን የሚዘጋበት አሰራር ሲሆን አሁን ግን በሶስቱ ሚዲያዎቻችን ላይ ተፈጽሞ ያየነው ፍጹም ከዩቲውብ ሕግና ደንብ ውጪ በሆነ ሁኔታ ሶስቱም ሚዲያዎቻችን ያለአንዳች ከሳሽና ያለአንዳች ማስጠንቀቂያ የተዘጉ መሆናቸው የተለየ ጉዳይ ያደርገዋል።
ሶስቱም ሚዲያዎች ኢትዮ 360 ሚዲያ ፣ አዲስ ድምጽ ራዲዮና ቴሌቪዥን እና ባሮ ቲውብ ቻናል ያለአንዳች ክስና ማስጠንቀቂያ ተዘግተዋል።
ሶስቱም ሚዲያዎች ሲዘጋባቸው ደግመው አዲስ ቻናል በመክፈት ስራ ሲጀምሩ እግር በእግር እየተከታተሉ ተደጋግሞ ተዘግቶባቸዋል።
ለምሳሌ ያህልም፦
� ኢትዮ 360 ሚዲያ 12 ግዜ አዲስ ቻናል ከፍተው ተዘግቶባቸዋል
� የጋዜጠኛ አበበ በለው አዲስ ድምጽ ራዲዮና ቴሌቩዥን ስድስት ግዜ እየከፈተ ተከታትለው ስድት ግዜ ዘግተውበታል።
� ባሮ ቲውብ ቻናል- እጅግ በአጭር ግዜ ውስጥ ስድስት ግዜ ከፍቶ ስድስቱንም ግዜ ተዘግቶበታል።
�ሶስቱም ሚዲያዎች ምንም አይነት ፕሮግራም ሳያስተላለፉ ገና « ሀ» ብለው አዲስ ቻናል እንደከፈቱ ዩቲውብ ተከታትሎ ዘግቶባቸዋል።
ይህንን ክስተት ስንመለከት ሶስት ሚዲያዎች - ማለትም ኢትዮ 360 ሚዲያ ፣ አዲስ ድምጽ ሚዲያና ባሮ ቲውብ ቻናል በድምር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰብስክራይበሮቻቸው ጋር ከዩቲውብ ሕግና ደንብ ውጪ እንደታገዱና ብሎም በስማቸው አዳዲስ ቻናል እንኴን መክፈት እንዳልቻሉ እንረዳለን ማለት ነው።
� ለዛሬው መልእክቴ መደምደሚያ- የዚህ ፔቲሽን አስፈላጊነትና ይህንን ለሚያነብ እያንዳንዱ ሰው ሚና ምን ያህል ወሳኝ መሆንን በተመለከተ በመግለጽ ይጠናቀቃል፦
ባለንበት 21ኛው ዲጂታል ክፍለ ዘመን መረጃ የመሪነቱን ስፍራ የጨበጠበት ዘመን ነው። የውሃ አቅርቦትን ያለቧንባ አቅርቦት ማሳካት እንደማይቻል ሁሉ የመረጃን ፍሰት ስኬታማ ማድረግ የሚቻለው የነጻነት እሴት ሲጠበቅ ብቻ ነው።
ዩቲውብ እራሱ የዚህ የዲጂታል ዘመን ተወላጅና ተፈጣሪ እንደመሆኑ መጠን የመናገር የመጻፍና ሀሳብን በነጻነት የማንሸራሸርን መብት ተቀብሎና አክብሮ የተፈጠረ ሀሳብ ማንሸራሸሪያ ግዙፍ ድርጅት ነው።
ድርጅቱ ከተመሰረተበት ዋና ዓላማና ከሚተዳደርበት የራሱ ሕገ ደንብ በተጻረረ መልኩ የአማራ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ነው ማረጋገጥ የቻልነው።
ይህ አይነቱ ስህተት ድርጅቱ ስራ ላይ ባዋለው የአልጎሪዚምና አርቲሪሻል ኢንተለጀንስ (AI) ማሺን ሲስተም የተፈጸም ሳይሆን በሰው ተቆጣጣሪዎች Human Controllers በኩል የተፈጸመ መሆኑን ነው ማረጋገጥ የተቻለው።
ይህ ማለት የዩቲውብ ድርጅት እራሱ - ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰብስክራይበሮች ያሏቸውን ሶስት ሚዲያዎችን አገልግሎት ያጣው እጅግ ውስን በሆኑ ጥቂት ሰራተኞቹ ምክንያት ነው ብለን እንድንረዳ አድርጎናል።
ስለዚህም ይህንን ዓይነቱን ውስጣዊን በደል ለማስቆም ፦
� ለዩቲውብ ዋና ጽ/ቤት
� ለአሜሪካን ፌዴራል ማሕበራዊ ኮምኒኬሽን ኮሚሽን
( Social Media | Federal Communications Commission of USA ) የሚገባ የአቤቱታ ማመልከቻ አዘጋጅተናል።
ሆኖም ይህ የአቤቱታ ማመልከቻ ሌጣውን ከሚገባ የእነዚህ ሚዲያዎቻችን አስፈላጊነትን ጠቃሚነትን የሚመሰከሩ ሰዎችን ፊርማ በማካተት ማቅረቡ ከሕግ ከሞራልና ከንግድም አንጻር ጠቃሚና አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህንን የፔቲሽን ማሰባሰቢያን ገጽ መክፈት የቻልነው።
ለዚህም ማግኘት የሚገባንን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ፊርማ በማግኘት የተነሳንበትን ዓላማ ለማሳካት የእናንት ትብብር መረባረብና መሳተፍ በእጅጉ ያስፈልጋል።
ያለእናንተ ተሳትፎ ፈጽሞ ምንም አይሰራም። ምንምም አይታሰብምም።
ውድ ወገኖች፦
ይህንን እሳቤን መሰረት በማድረግ በድጋሚ በአደራ ጥሪ የማደርገው በዚህ ፔቲሽን ላይ እስካሁን እንዳደረጋችሁት ርብርብ በሁሉም መስክ ተሳትፎን በማድረግ የታገዱብንን ሚዲያዎች ነጻ በማድረጉ ተግባር ላይ የበኩላችንን ድርሻና ሚናን እንድንወጣ በአክብሮት አደራ እላሉህ።
ሚዲያዎቻችንን እኛ ካልተከላከልን ማን ሊከላከልልን ይችላል?!!'
ከሰላምታ ጋር
ወንድወሰን ተክሉ ( ጋዜጠኛ)