የተወደዳችሁ ጓደኞቼ,
ወደ 23,000 የሚጠጉ ፊርማዎች ላይ ደርሰናል :: እናንተም ለዚህ ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ላደረጋችሁልን ከልብ የመነጨ ፈጣን ምላሽ በጣም የሚያስደንቅ እና የሚያረካ ነው :: በኛ በኩል እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው አሁን በመሆኑ በጀርመን ህግ መሰረት በጂጂ ኪያ ላይ ክስ ለመመስረት እየተዘጋጀን እና የወንጀል ጠበቆችን በመቅጠር እና ሰነዶችን እና ቪዲዮዎችን በማስተርጎም እየተዘጋጀን ነው:: ሆኖም ክሳችንን ከዳር ለማድረስ እና ለህግ ወጪዎች ድጋፍ እንዲሆነን እያንዳንዱ ሰው አቅም በፍቀደ ገንዘብ መዋጮ በመስጠት ተሳትፎ እንዲያደርግ ዕድል ለመስጠት ይህን የ GOFUNDME ገጽን አዘጋጅተናል :: የገንዘቡ አሠራር በአስተዳደሩ አራት አባላት ኮሚቴ ለግልፅ እና ትራንስፓረንት አኪያሄድ እንዲያመች ይከናወናል:: ማንኛውም የተረፈ ገንዘብ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት ወይም ሰውን በዘር፣ በሐይማኖት እና በቋንቋ እየከፋፈሉ ሀገርን ለማፍረስ የተነሱ ማንኛውም ዜጎችን ለህግ እንዲቀርቡ ለማድረግ ሌሎች ተመሳሳይ ምክንያቶችን ለመርዳት ወደ አንድ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በመስጠት ለበጎ ስራ ይውላል :: በተጨማሪም በሚቀጥለው የእኛን የFacebook ገጽ Bridges Ethiopia ( https://www.facebook.com/bridges.ethiopia.1 በመከተል ጥያቄዎችዎን እና ጥያቄዎትን የምንመልስበት ቦታ ላይ ይከታተሉን::
እንድትገነዘቡልን የምንፈልገው ነገር ቢኖር በጀርመን ሀገር ህግ መሰረት ጂጂ ኪያን እንከሳለን ነገር ግን ይህ ለፍርድ ውሳኔው ዋስትና አይሆንም:: ጂጂ ኪያ በጀርመን ህግ መሰረት እንከሳለን ልክ እንደ ማንኛውም የፍርድ ሂደትም, ለመተማመን ዋስትና መስጠት አንችልም:: ብቃት ያለው ጠበቃና ኣሳማኝ አሳማኝ ማስረጃዎችን እናቀርባለን:: ከብዙ በጥቂቱ ጂጂ ኪያ ሰውን በዘር በመከፋፈል በዘር ጥላቻ አንዱን ብሔር በሌላኛው ላይ የማነሳሳት ወንጀል በተግባር ፈጽማለች የወንጀል ሕገ-ደንብ ክፍል 1 (የጥላቻ ወንጀል) በክፍል 1 ውስጥ ተጠያቂነት ሊኖረው እንደሚችል ከህግ ባለሙያዎች ለማወቅ ችለናል . ይህ ደግሞ በጣም የከፋ ወንጀል በሚፈጠርባቸው ጊዜያት ከሦስት ወር እስከ አምስት ዓመት የእስራት ቅጣት ያስከትላል:: በተጨማሪም ፊርማዎን እና አስተያየቶቻችንን ለፍርድ ቤት አያይዘን እንልከዋለን ::
በተጨማሪ ገንዘቡን ስንሰበስብ ጓደኞቾ ፔቲሽኑን እንዲፈርሙ ያበረታቷቸው::
ስለትብብሮ እናመሰግናለን:: እባክዎን የሚቻለውን ያህል አስተዋጽዖ ያድርጉ::
ብሪጅስ ኢትዮጵያ
Dear Friends,
We have now reached almost 23,000 signatures. Your support and deep-felt commitments for this cause are very obvious and truly remarkable. It is time to act. We are now getting ready to launch a lawsuit on Gigi Kiya on German soil and are in the middle of translating documents and videos and employing a criminal lawyer. We are thus setting up this GOFUNDME page to give everyone a chance to contribute to this cause to pay for the legal expenses.
The management of your precious money will be handled by a committee of four people from Bridges Ethiopia who will account for each and every penny of the money raised. Any leftover money will be donated to a charitable organization to help Ethiopians or help other similar causes of bringing extremists to the law. You can also follow us on our FB page Bridges Ethiopia where we will answer your questions and queries.
Please be aware that while we are bringing a lawsuit on German soil, this does not guarantee a conviction. Gigi Kiya will be tried according to German Law, but like any trial, we cannot guarantee a conviction. We will hire the best possible lawyer and present the most convincing evidence. We do believe strongly and under advise of legal counsel that Gigi can be held accountable on the Volksverhetzung clauses (Incitement to Hatred) Section 1 of the Criminal Code, which can in worst offending cases carries a prison term of three months to five years. We will also submit your signatures and comments to the court of law. Encourage your friends to sign as we gather the funds to formally bring a case against Gigi Kiya. We thank you for your patience. Please contribute what you can.
Bridges Ethiopia