​የመርዝ ገበያ ይቁም! ለጤናማ ትውልድ ድምፃችንን በፊርማ እናሰማ!!

25

Let’s get to 50 signatures!
Petitions with 1,000+ supporters are 5x more likely to win!

The Issue

ወተት እንጠጣ" ወይስ "መርዝ"? የወተት ጥራት ቁጥጥር በአስቸኳይ ይጀመር!

​ዝርዝር መግለጫ (The Issue)፦

በሀገራችን የወተት ምርት ውስጥ መድኃኒት ያለበት ወተት ለገበያ እየቀረበ ይገኛል። ላሞች የታዘዘላቸውን የአንቲባዮቲክና የሌሎች መድኃኒቶች ማቆያ ጊዜ ሳይጨርሱ ወተታቸው ከጤነኛው ጋር ተቀላቅሎ ለህዝብ ይሸጣል። ይህ ደግሞ የመድኃኒት መላመድን (AMR) በማስከተል የትውልድን ጤና አደጋ ላይ እየጣለ ነው። በተጨማሪም እንደ ቲቢ (TB) ያሉ ተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥር ባለመኖሩ ህዝባችን ለከፍተኛ ስጋት ተጋልጧል።

​የምንጠይቃቸው መፍትሄዎች፦

​ማንኛውም ወተት ለገበያ ከመቅረቡ በፊት የመድኃኒት ቅሬታ ምርመራ እንዲደረግበት።
​በፋርሞች ውስጥ ያሉ ላሞች ለቲቢ እና ለሌሎች በሽታዎች በየጊዜው እንዲመረመሩ።
​የእንስሳት ህክምና ባለሙያዎች በፋርሞች ውስጥ ያለምንም ጫና ሙያዊ ውሳኔ እንዲሰጡ ከለላ እንዲደረግላቸው።

avatar of the starter
Volunteer Vet CarePetition StarterVolunteer Vet Care

Petition Updates