1 Million Signatures for Peace -1 ሚሊዮን ፊርማዎች ለሰላም

The Issue

  ይህ 1 ሚሊዮን ፊርማዎች ለሰላም ዘመቻ ትዉልድ ለሰላም የተሰኘውን ግዙፍ በሀገራችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የተቀረፀ ሀገር አቀፍ ኢኒሼቲቭ ወይም ፕሮግራም የመጀመሪያ ክፍል ሲሆን የፊርማ ማሰባሰቢያዉ ትዉልድ ለሰላም ፕሮግራም በህብረተሰቡ ዘንድ ድጋፍና እዉቅናን እንዲያገኝ ለማድረግ በማሰብ የተዘጋጀ ነው።

 የዘመቻዉ አላማ ለፕሮግራሙ ከመላዉ የኢትዮጵያ ህዝቦች በትንሹ አንድ ሚሊዮን የድጋፍ ፉርማዎችን በአካልና በኢንተርኔት በማሰባሰብ  ትውልድ ለሰላም ኢኒሼቲቭን እንደሚደግፉ በፊርማቸዉ የሚያረጋግጡበት እንቅስቃሴ ነዉ፡፡
በተጨማሪም ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በትንሹ 1 የሰላም መልዕክት በተለያዩ መንገዶች እንዲያስተላልፉ በማድረግ
ህብረተሰቡን ለሰላም መቀስቀስ ነዉ!

ትዉልድ ለሰላም 

ትዉልድ ለሰላም ኢኒሼቲቭ ከተለያዩ ፊልዶች ከተዉጣጡ ባለሞያዎች በተመሰረተ 6 አባላት ባሉት ቡድን
በሀገራችን በተደጋጋሚ እየተስተዋሉ ላሉት ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የተዘጋጀ በሁሉም የኢትዮጵያ
ክልልሎችና በሁለቱ የከተማ መስተዳደሮች ተግባራዊ የሚደረግ ትልቅ ፕሮግራም ነዉ፡፡
የፕሮግራሙ መነሻ ሀሳብ ምንም እንኳን ሰላምን በማስፈን ረገድ መንግስት ጉልህ ድርሻ ቢኖረዉም ሰላም
በሚደፈርስበት ወቅት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚጎዳዉ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በመሆኑ የግጭቶች ዋነኛ
ተጠቂ የሆነዉን ህብረተሰብ ወደ መፍትሄ አካልነት ለማሸጋገር በማቀድ ነዉ፡፡ በሀገራችን ሰላምን ማስፈን እንደ ዜጋ
የሁላችንም የጋራ የቤት ስራ መሆኑን በማመን እንዲሁም የሰላም ጉዳይ በጥቂት የፖለቲካ ልሂቃንና የመንግስት
ዉይይት ብቻ የሚወሰን አለመሆኑን ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት ከተለመደዉ ለየት ባለ መልኩ ህዝብ ተኮር ሆኖ
ተዘጋጅታል፡፡
ይህ ፕሮግራም በዉስጡ ብዙ ፕሮጀክቶችን ያቀፈ ሲሆን በተለየ መልኩ የህዝብ ድምፅ ጎልቶ እንዲሰማና
ህብረተሰቡ በሰላም ግንባታዉ ዘርፍ ጉልህ ድርሻ እንዲኖረዉ የሚያስችል ነዉ፡፡ለየትኛዉም የፖለቲካ ፓርቲ
የማያዳላ፤ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ብሄሮች ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዘር፤ በሀይማኖት፤ በፆታ፤ በቀለም፤
በፖለቲካ አቅም፤ በማህበራዊ ደረጃና በኢኮኖሚ አቅም ሳይለይ እኩል የሚያሳትፍ ፕሮግራም ሲሆን፡ የማህበረሰቡን
አመለካከቶች፤ ጥያቄዎች፤ ቅሬታዎች እሴቶች፤ባህሎች፤ታሪኮች፤እምነቶች፤ ትዉፊቶች፤ የመፍትሄ ሀሰቦች
የሚያንፀባርቅ ሂደትን ይከተላል፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘዉ የጋራ ችግሮቻቸዉን በጋራ
የሚለዩበትና ለጋራ ችግሮቻቸዉ የጋራ መፍትሄ የሚፈልጉበት በግልፅነትና በአሳታፊነት ላይ የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ
ነዉ፡፡

የትውልድ ለሰላም ኢኒሼቲቭ ግብ ራእይ እና አላማዎች 

ግብ

በኢትዮጵያዊያን ህዝቦች መካከል በጋራ ችግር በመለየትና መፍትሄ በመስጠት ሂደት መተማመንና መተባበር የሚፈጠርበትን መድረክ ማዘጋጀት
ተልዕኮ
ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች ለሰላም ግንባታ የድርሻቸዉን የሚያበረክቱበት እና የሁሉም ሀሳብ የሚንፀባረቅበት መድረክ በማዘጋጀት ለዘላቂ ሰላም መሰረት መጣል
ራዕይ
ጠንካራ፤ ሰላማዊ የሆነና ልዩነቶቹን በዉይይትና በምክክር የሚፈታ ትዉልድን መፍጠር
አላማ
ምክክሮችን፤ ዉይይቶችን፤ ክርክሮችን፤ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያካተተ የፓርቲሲፓቶሪ አክሽን ሪሰርችን በመጠቀም በዉስጡ የሰላም፡ የማህበራዊ ጉዳዮች ፤የኢኮኖሚ ጉዳዮች፤ የፖለቲካ ጉዳዮችን ያካተተ ሁለገብ ብሄራዊ ፍኖተ ካርታ በመቅረፅ ዘላቂ ሰላም ማምጣት
ዝርዝር አላማዎች
1. በአንገብጋቢ የሰላም ጉዳዮች ላይ በሰፊ ክርክርና ዉይይት የተቀረፀ የምርምር ዉጤትን ይፋ ማድረግ
2. የግጭቶችን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ታሪካዊ፡ ፖለቲካዊ ምንጮች መለየት የሚያስችል አካታች የሰላም ፕሮግራም መቅረፅ
3. በህብረተሰብ ተሳትፎ ላይ የተመሰረቱ የህግና የፖሊሲ አቅጠጫዎችንና መፍትሄዎችን ማስቀመጥ
4. በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል መካከል መተማመንን መፍጠርና ማሳደግ
5. በአጠቃላይ የህብረተሰቡን፤ በተለይ ደግሞ የወጣቶችንና የሴቶችን ልዩነቶችን በሰላም የመፍታት ብቃትና ተሳትፎ ማሳደግ
6. ሰላምን ለማስፈን የንግግርና የዉይይት ባህልን መፍጠርና ማዳበር
7. የግጭቶችን መንስኤዎች በመለየትና መፍትሄ በመስጠት በብሄር ብሄረሰቦች መካከል ያለዉን የሻከረ ግንኙነት ማሻሻል
የፕሮግራሙ ሂደት
የትዉልድን ለሰላም ፕሮግራም በአይነቱ ለየት ያለ ፓርቲስፓቶሪ አክሽን ሪሰርች የተሰኘ ተግባር ተኮር የሪሰርች/የጥናት አይነት የሚጠቀም ሲሆን የጥናት/የሪሰርች እና የተግባር/ አክሽን ክፍል ይኖረዋል!

ሀ. የፕሮግራሙ የጥናት ክፍል
የፕሮግራሙ የጥናት ክፍል በበኩሉ ሁለት ክፍሎች ይኖሩታል! የግጭት መንስኤዎች ጥናትና የመፍትሄዎች ጥናት
1. የፕሮግራሙ የግጭት መንስኤ ጥናት ክፍል
የሰላም ሂደቱ ከተለመደዉ በተዘጋ በር በልሂቃን ብቻ የሚደረግ ዉይይትና ምክክር በመሻገር ሁሉንም የማህበረሰብ
ክፍል በሁሉም ክልሎች ያለፍርሀትና ተፅእኖ በወንድማማችነት ስሜት አብሮ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊና
ታሪካዊ የግጭት መንስኤዎች ላይ በባለሞያዎች እየታገዘ ጥናት/ሪሰርች የሚያደርግበትን ሂደት ይፈጥራል፡፡ ጥናቱ
የሚካሄደዉ ከቀበሌ ጀምሮ በሚደረጉ አካታችና አሳታፊ ዉይይቶች ሲሆን በዉይይቶቹ ህብረተሰቡ እንደልቡ
ጥያቄዎቹን የሚጠይቅበት፤ ሀሳቡን፤ ቅሬታዎቹንና ስጋቶቹን በሰላማዊ መንገድ የሚገልፅበት መድረክ ይፈጠራል፡፡
በዚህ የግጭቶችን መንስኤ ለማወቅ በሚደረጉ ጥናቶች አብሮ የመስራት ሂደት ማህበረሰቡ እንዲሁም የተለያዩ
ቡድኖች ለአንድ አላማ በመወያየትና በመመካከር ሲሰሩ አንዱ የሌላዉን ችግር የተሻለ እየተረዳና የሻከረ
ግንኙነታቸዉ እየተሸሻለና እየታከመ ይመጣል፡፡
2. የፕሮግራሙ የመፍትሄ ጥናት ክፍል
ሁለተኛዉ የጥናት ክፍል ህብረተሰቡ ዉይይቱን በመቀጠል በባለሞያዎች እየታገዘ እራሱ ለለያቸዉ የግጭት
መንስኤዎች የመፍትሄ ሀሳቦችን የሚያመነጭበት ሂደት ነዉ፡፡
የመፍትሄ ሀሳቦች ጥናቱ ካለቀ በሃላ በህብረተሰቡ በጋራ የተሰራዉ የግጭት መንስኤዎች ጥናትና የመጡት
የመፍትሄ ሀሳቦች በሪፓርት መልክ በፈርጅ በፈርጁ ተዘጋጅተዉ ለሲቪክ ማህበራትና ለፖለቲካ ልሂቃን እንዲሁም
ለመንግስት ይቀርባሉ፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚዘጋጁ ትልልቅ የምክክር መድረኮች የሲቪክ ማህበራት፤ የፖለቲካ
ልሂቃንና መንግስት በበኩላቸዉ ህብረተሰቡ ከታች ጀምሮ እየለየ ያመጣቸዉ የግጭት መንስኤዎችና የመፍትሄ
ሀሳቦች ላይ ተመርኮዘዉ ተጨማሪ ግጭት ሊያመጡ የሚችሉ ችግሮችን ከራሳቸዉ አንግል እንዲለዩ ይደረጋል፡፡
በዚህም ሂደት ሲቪክ ማህበራት እንደ ሲቪክ ማህበራት፤ የፓለቲካ ልሂቃን እንደ ፓለቲካ ልሂቃን እንዲሁም
መንግስት እንደ መንግስት ያሉባቸዉን ችግሮች ያለምንም ተፅአኖ እንዲለዩ ይደረጋል፡፡
በመቀጠልም ህብረተሰቡ ለለያቸዉ የግጭት መንስኤዎችና እራሰቸዉ የሲቪክ ማህበራትና የፖለቲካ ልሂቃን
ለለዩዋቸዉ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ታሪካዊ የግጭት መንስኤዎች በፅሁፍ ፕሮፖዛል መልክ የመፍትሄ
ሀሳቦችን ያዘጋጃሉ፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መንግስትና ተፎካከሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች
አንዲሁም ልሂቃን ለጋራ ችግሮቻቸዉ የጋራ መፍትሄ የሚፈልጉበት በቃላትና በመሳሪያ ሳይሆን የተሻለ ሀሳብ
ለማምጣት በሰላም የሚፋለሙበት የምክክር መድረኮች ይዘጋጃሉ፡፡
ለ. የፕሮግራሙ የተግባር ክፍል
የፕሮግራሙ የተግባር ክፍል በበኩሉ በህብረተሰብ ደረጃ የሚወሰድ ተግባርና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወሰድ ተግባር
የተሰኙ ሁለት ክፍሎች ይኖሩታል፡፡ 

1. በህብረተሰብ ደረጃ የሚወሰድ ተግባር
በህብረተሰብ ደረጃ ያሉ አለመግባባቶቹን ከስር በተሰጡት የመፍትሄ ሀሳቦች መሰረት እንደ ሽምግልና እና ኔጎሼሽን
የመሳሰሉ ዘመናዊና በየክልሉ በታወቁ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም መፍታትና ክልላዊ የሰላም
ስምምነቶችን መፈራረም
2. በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወሰድ ተግባር
በአ.አ. በአይነቱ ለየት ያለ በተግባር ሊረጋገጥ በሚችል የችግሩ ባለቤት በሆነዉ በራሱ በህብረተሰቡ በተሰራ
ሪሰርች/ጥናት ላይ የተመሰረተ የምክክክር መድረክ ይዘጋጃል፡፡ዉይይቱ የሚደረገዉ ከስር በማህበረሰቡ የተጠኑት
እንዲሁም በሲቪክ ማህበራት ፤ በፖለቲካ ልሂቃንና መንግስት የተለዩ የግጭት መንስኤዎችና መፍትሄዎች ላይ
ተመስርቶ ሲሆን በዉይይትና በክርክር ከተለዩት መፍትሄዎች መካከል የትኞቹ በህጎች፤ በፖሊሲዎችና በፐብሊክ
ፕሮግራሞች መልክ ተቀርፀዉ ተግባራዊ መሆን እንዳለባቸዉ የሚወሰንበትና ለሀገሪቱ የጋራ መጪ ጊዜ የጋራ ራዕይ
እና የማህበራዊ፡ ኢኮኖሚያዊ፤ የፖለቲካዊና፡ የታሪካዊ ዘርፎች ያሉት ብሄራዊ ፍኖተ ካርታ የሚቀረፅበት ሂደት ነዉ፡፡
የተቀረፀዉ ፍኖተ ካርታ በተለያዩ ተቀማትና መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ተግባራዊ የሚደረግ
ሲሆን ተፈፃሚነቱን የሚቆጣጠር ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የተዉጣጣ አካል ይኖረዋል፡፡
ትዉልድ ለሰላም ኢኒሼቲቭ ከሰላም ሚነስቴር በተጨማሪ እንደ የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት፡ የሐይማኖት
ተቀማት ም/ቤት፡ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት፤ የወጣቶች ካዉንስል፤ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን፤ የሴቶች
የሰላም ም/ቤትና ከተለያዩ ሀገር በቀልና አለም አቀፍ ሲቪክ ማህበራትና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ለመስራት
ያቀደ ሲሆን አብሮ የሚሰራቸዉን ተቀማት በቀጣይ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ይፋ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
በአጠቃላይ የትዉልድ ለሰላም ኢኒሼቲቭ ለ 9 ወራት የሚቆይ ሲሆን ፕሮግራሙን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀዉና ነሀሴ 29 ቀን 2012  በጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ የሆነው  የ 1 ሚሊዮን ፊርማዎች ለሰላም ዘመቻ  ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት የሚቆይ ይሆናል፡፡ ዘመቻዉ
ከፊርማ ማሰባሰብ በተጨማሪ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴዎችም ይኖሩታል፡፡
በመሆኑም መላዉ ኢትዮጵያዊያን ይሄንን የህዝብ የሰላም ፕሮግራም በመደገፍና ከጎናችን በመቆም ለመጪዉ
ትዉልዶች ሰላምን እንዲያወርሱ አደራ እያልን፤ ከአሁን ጀምሮ በተዘጋጀዉ የፊርማ ማሰባሰቢያ ፊርማቸዉን
እንዲያኖሩ በፍቅር እንጠይቃለን!
በዚህ አጋጣሚ መጪዉ ዘመን 2013 በሰላም፤ በፍቅርና በጤና የተሞላ እንዲሆን እየተመኘን ህዝቡም እርስ በእርሱ
የሰላም መልዕክቶቹን እንዲያስተላልፍ እንጋብዛለን!
ፈጣሪ ሀገራችንንና ህዝቦቸን ይባርክ

avatar of the starter
Saron LisaneworkPetition StarterA Researcher and Master of Laws (LL.M) graduate from University of South Africa with specialization in Fundamental Rights.
This petition had 7,714 supporters

Petition Updates

Share this petition

Petition created on November 3, 2018