Actualización de la peticiónUphold Freedom of Expression and Fair Treatment for Ethiopian Amhara Mediasየኢትዮ 360 ሚዲያ፣የአዲስ ድምጽ ሚዲያና የባሮ ቲውብ ቻናል ሰብስክራይበሮች 10% ፊርማ ይፈለጋል-በፔቲሽኑ ተሳተፉ
Wondwossen TekluNairobi, Kenia
21 sept 2023

ስርዓቱ ሚዲያዎቻችን ከዩቲውብ ላይ ከማሳገድ ወደ ከሳተላይት ላይ የማስወረድ ዘመቻ ጀምሯል-የዩቲውብን ሕገወጥ እገዳን ለማንሳት በዚህ ፊርማ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ላይ ነና ሁላችሁም ተሳተፉ!!!

 

ውድ ወገኖች

ከሁሉም በማስቀደም  ወርቃማ ጊዜያችሁን ሰውታችሁ በዚህ በፊርማ የማሰባሰቢያ (ፔትሽን) ዘመቻ ላይ ለተሳተፋችሁና ዛሬም ሆነ ነገ - የፔትሺኑ ዘመቻ እስኪጠናቀቅ ድረስ ማለት ነው ለምትሳተፉ ቅን ኋላፊነት የሚሰማችሁ ወገኖቻችን በሙሉ ልባዊ የአክብሮት ምስጋናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

በዚህ የፊርማ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ላይ ላልተሳተፋችህ ውድ የኢትዮ 360 ሚዲያ፣የአዲስ ድምጽ ሚዲያ፣የባሮ ቲውብ ቻናል ወዳጆች ሰብስክራይበሮችና ብሎም ሀሳብን በነጻነት መግለጽ በምታምኑ ወገኖች በሙሉ በዚህ ዘመቻ ፊርማዎን በማኖር ሊንኩን በማጋራትና በማሰራጨት እንድትሳተፉ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።

ኦህዴድ መራሹ የኦሮሙማው ፋሺስታዊው ቡድን በርካታ ሚዲያዎችን ከዩቲውብ በዘመቻ ማሳገዱን ታውቃላችሁ። ቡድኑ በዚህም ሳያበቃ ዛሬ ኢትዮ 360 ሚዲያ ፣አዲስ ድምጽ ሚዲያንና መረጃን ከሳተላይት ቻናል ላይ አውርዶ ሕዝባችንን መረጃ አልባ በማድረግ የከፈተውን የጭፍጨፋን ጦርነት ለማሳለጥ ሲጥር እየታየ ነው።

እነሱ ሲያዘጉ እኛ ደግሞ የማስከፈት ዘመቻን ከፍተን የተዘጉብንን ማስከፈትና እንዳይዘጉ ማድረግ ይኖርብናልና እነሆ ይህንን  UNBLOCK ETHIO 360 MEDIA ADDIS DIMTS MEDIA BARO TUBE CHANNEL - BY SIGNING THIS PETITION የሚል ፊርማ ማሰባሰቢያ ፔቲሽን ልንከፍት ችለናል።

 

1ኛ. የዚህ ፔቲሽን ዓላማና ጎል፦

የዚህ ፔቲሽን ዓላማና ጎል የዩቲውብ ድርጅት ከሚመራበት የራሱ ሕግና ደንብ ውጪ በሆነ ሁኔታ ስርጭታቸውን ያገደባቸውን ሚዲያዎቻችንን ኢትዮ 360 ሚዲያ፣ አዲስ ድምጽ ሚዲያና ባሮ ቲውብ ቻናሎች ሕገወጥ እገዳ እንዲነሳ ማድረግና ሚዲያዎቹ ዳግመኛም ለእንደዚህ ዓይነቱ ሕገ ወጥ አፈና ሰለባ እንዳይሆኑ ማድረግ ነው።

 

2ኛ. የዚህ ፔቲሽን ጥቅምና አስፈላጊነት ምን ያህል ነው ?? የእናንተስ ፊርማና አስተዋጾኦ ምን ያህል የሚፈለገውን ለውጥ ሊያመጣ ይቻለዋል?

ሶስቱ ሚዲያዎቻችን ማለትም ኢትዮ 360 ሚዲያ አዲስ ድምጽ ሚዲያና ባሮ ቲውብ ቻናል በድምሩ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋን ሰብስክራይበሮችን በእለታዊ ዜና እለታዊ ትንታኔን በማቅረብ  የሚዲያ አፈና ባለባት ሀገራችን ለሚሊዮኖች አማራጭ ድምጽ በመሆን እያገለገሉ ያሉ የሕዝብ ድምጾች ናቸው።

ለዩቲውብ ድርጅትና   ለአሜሪካው Social Media | Federal Communications Commission. ቢሮ የሶስቱን ሚዲያዎቻችን ሰብስክራይበሮች ውስጥ ቢያንስ 10% ያህሉን የድጋፍ ፊርማ ያለበትን ማመልከቻን በማስገባት የሚዲያዎቻችንን የሽፋን ስርጭት ስፋትና የሚዲያዎቻችን በአድማጭ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት ማረጋገጫ ሆኖ ከሕግ አንጻር ብዙ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጣ ተሳትፎ ከእናንተ የሚፈለግ መሆኑን ማወቁ ተገቢ ነው።

 

3ኛ. ለኢትዮ 360 ሚዲያ፣ ለአዲስ ድምጽ ሚዲያና ለባሮ ቲውብ ቻናል ሰብስክራይበሮችና ወዳጆች በመሉ፦

እናንተ የሶስቱ ሚዲያዎቻችን ሰብስክራይበሮችና ወዳጆች በሙሉ ከማንኛውም ተሳታፊ በላይ ትልቁን የኋላፊነት ግዴታ በትከሻችሁ ላይ የያዛችሁ መሆኑን እንድታውቁት እንወዳለን።

የሶስቱ ሚዲያዎች ድምር ሰብስክራይበሮች ብዛት  ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ሲሆን ከዚህ ውስጥ በትንሹ የ10% ያህሉን ሰብስክራይበሮችን ፊርማ በዚህ ፔቲሽን ላይ ማሰባሰብ ይኖርብናል።

 

4ኛ. በትንሹ 10% ያህል የሶስቱን ሚዲያ ሰብስክራይበሮችን ፊርማ እንፈልጋለን፦

 

 በዚህም መሰረት ዛሬ በትንሹ የ10% ያህሉን የኢትዮ 360 ሚዲያ፣የአዲስ ድምጽ ሚዲያና የባሮ ቲውብ ቻናል ሰብስክራይበሮችን ፊርማ በዚህ ፔቲሽን መሰብሰብ  ቢቻል  ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚቻለን ለመግለጽ እንወዳለን።

ስለሆነም  የሶስቱ ሚዲያ ሰብስክራይበሮችና ደጋፊ የሆናችሁ በሙሉ በዚህ ፔቲሽን የማሰባሰቢያ ዘመቻ ላይ  የመሳተፍ ሞራላዊና ኋላፊነታዊ የውዴታ ግዴታ እንዳለባችሁ አውቃችሁ ፊርማችሁን በማኖር ሊንኩን በማጋራት በማሰራጨትና ላላወቁት ወዳጅ ቤተሰብ አሳውቆ  እንዲሳተፉ በማድረግ ወሳኙን ሚና እንድትወጡ በአክብሮትና በፍቅር ጥሪ አድርገናል።

ስለተሳትፏችሁ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን!

ስንተባበር ለውጥ እናመጣለን!!

ከአክብሮት ምስጋና ጋር

 

 

Apoya la petición ahora
Firma esta petición
Copiar enlace
WhatsApp
Facebook
Nextdoor
E-mail
X