Actualización de la peticiónUphold Freedom of Expression and Fair Treatment for Ethiopian Amhara Mediasያለመናገር ደጃዝማችነትን ያስቀራል -ለመላው ነጻነት አፍቃሪዎችና አክባሪዎች የተላለፈ የተሳትፎ ጥሪ
Wondwossen TekluNairobi, Kenia
15 sept 2023

ያለመናገር ደጃዝማችነትን  ያስቀራል

ለመላው ነጻነትን አፍቃሪና አክባሪ ለሆናችሁ ውድ ወገኖች የተላለፈ የተሳትፎ ጥሪ፦

 

ውድ ወገኖች፦

 

ያለንበትን 21ኛውን የዲጂታል ዘመን ብዙዎች ወርቃማው የሰው ልጅ ዘመን እያሉ ይጠቅሱታል። ወይም ወደ ወርቃማው የሰው ልጅ ዘመን አሸጋጋሪ ድልድይ ሲሉም ይገልጹታል። ይህ የዲጂታል ዘመን መረጃ በብርሃን ፍጥነት ከምድር አጽናፍ እስከአጽናፍ በመድረስ ስልጣኔን እውቀትን ጥበብንና ቴክኖሎጂን በማስፋፋት ላይ በመሆኑ ነው ወርቃማው የብርሃን ዘመን እየተባለ የሚገለጸው።

 

በዚህ ብርሃናማው የመረጀ ዘመን ሕዝባችንና ሀገራችን የኋይል ምንጭ የሆነውን መረጃን እንዳይደርሰው ታፍኖና ታግዶ ያሉበት ሁኔታን ስናይ እያንዳንዳችን በሀገራችን ኢትዮጲያ ላይ የተጣለውን የአፈናን ተግባር ኡንዴት እናንሳው ብለን እንድንጠይቅና እንድንቀሳቀስ አድርጎናል። ወይም እንድንቀሳቀስ ያስገድደናል።

 

ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰብስክራይበሮች መብት ተጥሷል። የኢትዮ360 ሚዲያ የአዲስ ድምጽ ራዲዮና ቴሌቪዥንና የባሮ ቲውብ ቻናል ድምር ሰበስክራይበሮች ሚሊዮን ይደርሳሉ። ዩቲውብ ያለአንዳች ማስጠንቀቂያና ጥፋት እራሱ ካስቀመጠልን Community Guidelines Rules and Regulations ውጪ ሶስቱን ሚዲያዎችን ጨምሮ በርከት ያሉ ሚዲያዎችን አግዷል።

 

ኢትዮ 360 ሚዲያ ከ15 ግዜ በላይ በአጭር ግዜ ውስጥ ታግዷል። አዲስ ድምጽና ባሮ ቲውብ ቻናል ከስምንት ግዜ በላይ በተመሳሳይ ግዜ ታግደዋል።

 

 

አላማው በጦርነት ስር ያለውን የአማራን ሕዝብ መረጃ መንሳት። ጦርነት የተከፈተበትን የአማራን ሕዝብ ድምጽ የማፈን ተግባር መፈጸም ነው።

ፋሺስታዊው የኦሮሙማው ስርዓት ይህንን የአፈና ዘመቻን ለማሳለጥ ከፍተኛ በጀት መድቦ ግሩፕ ፈጥሮ በመስራት ላይ ይገኛል።

 

እኛ በሰው ልጅ ነጻነት የምናምን ከሆነ በዚህ በወርቃማው ብርሃናማ የመረጃ ዘመን ውስጥ የመረጃ ምንጮቹን ተነጥቆ በጨለማ ላለው ሕዝባችን ድምጾቹ ይመለሱለት ዘንድ የዩቲውብ ድርጅት እየፈጸመ ያለውን ሕግና ደንብ ያልተከተለን እርምጃውን በሕግና ደንብ በመጠየቅ ልናስቆመው ይህንን ፔቲሽን ከፍተናል።

 

በፔቲሽኑ ላይ የእያንዳንዳችን ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ ነው። ምክንያቱም ለዩቲውብ ድርጅት እና በአሜሪካን ለማሕበራዊ ትሥስር ገጾች ኮሚሽን ቢሮ ለምናስገባው ሕጋዊ የመብት ጥያቄ የእያንዳንዳችሁ ፊርማ ያስፈልጋል። ይጠቅማልም።

 

ስለዚህ እስካሁን ድረስ ከአራትሺህ የበለጠ ፊርማዎችን ማሰባሰብ መቻሉን በመግለጽ እና በዚህም ለተሳተፋችሁ በሙሉ ጥልቅ ምስጋናን እየገለጽን  እስካሁን ፊርማችሁን ያላኖራችሁ የነጻነት አፍቃሪና አክብሪዎች በዚህ የፊርማ ማሰባሰብ ተግባር ላይ ፊርማችሁን በማኖር የፔቲሽኑን ሊንክ ለወዳጅ ዘመድ ቤተሰብና የተለያዩ ኔትወርኮቻችሁ ላይ በማጋራትና በማሰራጨት እንድትሳተፉ በአክብሮት ጥሪ አቅርበናል።

 

ያለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል።

ከአክብሮት ምስጋና ጋር

Apoya la petición ahora
Firma esta petición
Copiar enlace
WhatsApp
Facebook
Nextdoor
E-mail
X