Open letter to the Prime Minster of Ethiopia on legitimate demands of Physicians

The Issue

ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት 

ጉዳዩ :- መብታችንን ስለመጠየቅ ይሆናል

እኛ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች በከፍተኛ የትምህርት ጫና አልፈን ሀገሪቷ ውስጥ ባሉ ጤና ተቋማት ተመድበን እየተማርንና እየሰራን እንገኛለን። ያሉብን እጅግ በጣም ችግሮች እንዲስተካከሉ ለተለያዩ ሴክተር ሀላፊዎች በተደጋጋሚ የጠየቅን ቢሆንም ቃል ከመግባት ባለፈ ምንም ሳይስተካከል ለዘመናት ታግሰን ቆይተናል። አሁን ግን ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ብሎም ሐኪሞች ላይ ያለው ጫናና ክብረነክነት እስከ ዱላ መሰናዘር ድረስ ስለደረሰ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መብታችንን ለማስከበር ቆርጠን ተነስተናል። ስለሆነም የሚከተሉት ችግሮች በ 2 ወር ጊዜ ውስጥ እንዲስተካከሉልን እየጠየቅን ጥያቄዎቻችን የማይመለሱ ከሆነ ግን እንደ ቤተሰብ ከምናያቸ ታካሚዎቻችን ርቀን ስራ ለማቆም እንገደዳለን::

1. እኛ ስራችን ከተከበረው የሰው ልጅ ህይወት ጋር የተያያዘ በመሆኑ እጅግ ተጨንቀን ተምረን እጅግ ተጨንቀን ደፋ ቀና እያልን እየሰራን ማንም ሊያምን በማይችል መልኩ ከአገልግሎታችን የማይመጣጠን ክፍያ እየተከፈለን ስለሆነ ከኑሮ ውድነት ጋር አልመጣጠን ብሎን በንጹህ አኧምሮ ታካሚዎቻችን እንዳናክም አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረብን ይገኛል ::አውሮፓና ኣሜሪካ ያለውን የደመወዝ ስኬል ቀርቶ ጎረቤቶቻችን ሱዳንና ኬንያ የሚከፍሉት ደሞዝ ከእኛ ሐገር ደሞዝ ጋር ሰማይና ምድር ነው። ስለዚህም ሙያችን ና አገልግሎታችን ያማከለ የደሞዝ ጭማሪ ይደረግልን::

2. ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች (ቲቢ ፣ ሄፕታይተስ ቢ ና ሲ ቫይረስ ፣ ኤችአይ ቪ ወ ዘ ተ) ተጋላጭ መሆናችን የአደባባይ ሚስጥር ነው። ነገር ግን የተጋላጭነት :የቤት ኪራይ እና የሙያ አበል እየተከፈለን ያለው ክፍያ ለሃገሪቷ እጅግ አሳፋሪ ነው:: ይህ በአስቸኳይ ይስተካከልልን ::

3. ከየ ዪኒቨርሲቲዎች ተመርቀን ክሊራንስ ጨርሰን ስንወጣ ያለብንን የመንግ ስት እዳ ምንፈርመው 43000 የኢትዮጵያ ብር አይሞላም። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች የትምህርት መረጃችን ለመውሰድ ስንፈልግ ምንም በማናቀው ምክንያት ሌሎች ተጠይቀው ማያቁትን ግማሽ ሚሊየን ብር መጠየቃችን አግባብነት ስለሌለው እኛ በፈረምነው ገንዘብ ልክ ከፍለን የትምህርት መረጃችን መውሰድ እንዳንችል ምንጠየቀውን የተጋነነ ክፍያ ይቁምልን::

4. አንድ ሐኪም ለታካሚው ጥሩ ህክምና ለመስጠት ጤነኛ የስራ አካባቢ : የተሟላ የህክምና መሳሪያ ያስፈልገዋል እኛ ግን በስርዓት ጓንት እንኳን የማይገኝበት ፡ ደህንነታችን የማይጠበቅበት :ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ ቦታዎች ላይ የተሰሩ ተቋማት ውስጥ እየሰራን እንገኛለን። ይህ ደግሞ ያለንን እውቀት ተጠቅመን ማህበረሰቡን ለማገልገል ሳንካ ሆኖብናል :: የመንግስት ችግር መሆኑን ህዝቡ ስለማያውቅ ከህመሙ ካልዳነ ከኛ አቅም በላይ በሆነው ምክንያት እንወቀሳለን: እንሰደባለን፡ እንደበደባለን :የስነ ልቦና ጫናም ይደርስብናል :ስማችን በየመገናኛ ብዙሃን ይጠፋል: : ስለሆነም መንግስት በአፋጣኝ እነዚህን ችግሮ ች እንዲያስተካክልልን ማለትም በየጤና ተቋማት በቂ እና አስፈላጊ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እንዲሟሉ ፡ የመኖሪያ አካባቢያችን ምቹ እንዲሆኑል ና ደህንነታችን እንዲጠበቅልን እንጠይቃለን።

5. ሐኪሞች የሰው ልጆች እንደመሆናችን መጠን የማህበረሰቡን ጤና ልንጠብቅ የምንችለው የኛ ጤና ና ደህንነት ሲጠበቅ ነው ። እጅግ ተቸግረን ለመኖር መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ማሟላት በማንችልበት የድህነት ወለል በታች መኖር ይብቃን ! መኪና ከቀረጥ ነጻ ማስገባት ምንችልበት ፡ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የምንሆንበት፡ ኢኮኖሚያችን የምናሻሽልበት የባንክ አገልግሎት የምናገኝባቸው መንገዶች ይመቻችልን ።

6. እኛ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች እንድናክም እንጂ እንዳንታከም ተፈርዶብናል !ይህ ችግር ተቀርፎ እስከ ውጭ ሃገር መታከም እንችል ዘንድ የጤና ኢንሹራንስ እንዲኖረን እንፈልጋለን።

7. እኛ የኢትዮጵያ ሐኪሞች ዓለም ላይ ካሉ ሐኪሞች በምንም መስፈርት አናንስም !USMLE center አገራችን ውስጥ ተከፍቶልን አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ሃኪም የምንሆንበት መንገድ ይመቻችልን።

8, አገራችን ውስጥ በሚረቀቁ ፖሊሲዎች ላይ የመሳተፍ ችሎታውም እውቀቱም እያለን ሃኪሞችን ያላካተተ ፖሊሲ ሳናምንበት በግድ ተጭኖብን ልንቀበል አይገባም ። ስለዚህ ያለ ችሎታቸውና የትምህርት ደረጃቸው በየጤና ሴክተሩ በዘመድ ና በመተዋወቅ የተሰገሰጉ አመራሮች ሙሉ በሙሉ በወጣት:በሳል ፡የማህበረሰቡን ጤና በቅጡ በተረዱ ፡ በቂ ችሎታ ባላቸው የሐኪም አመራሮች ከቀበሌ እስከ ፌደራል ድረስ ይቀየሩ።

9, በየህክምና ኮሌጆች አግባብነት የሌለው የኢንተርን ሐኪሞች የጉልበት ብዝበዛ ና የስነ ልቦና ጫና ፡ የህክምና ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና ስቃይ 1 ትምህርት ውጤት ሲበላሽባቸው 2 እና ከዚያ በላይ አመታትን ሚደግሙበትን አሰራር ተቀይሮ እንደማንኛውም ተማሪ ድጋሚ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ሚያሻሽሉበት ሁኔታ ይፈጠርልን። ፈተናውም እውቀትና ችሎታን ያማከለ እንጂ ፈታኞች በግላዊ ስሜትና ጥላቻ የማይወስኑበት ይሁንልን።

10. ኢትዮጵያ ከ መቶ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ሀገር ናት። ለዚህም ብዙ ስፔሻሊስቶችና ሰብ ስፔሻሊስቶች ያስፈልጋሉ ። ጠቅላላው የሐገሪቱ ሃኪሞች ስፖንሰር ለማግኘት ከክልል ክልል እና ከተቋማት ተቋማት ይለያያል። ይህ ደግሞ ኢ-ፍትሃዊ ስለሆነ ሁሉንም ሃኪሞች ትምህርት ሚኒስቴር ወጥ በሆነ መልኩ ስፖንሰር ሆኖን ተምረን ሃገራችን በህክምናው ዘርፍ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ይረዳን ዘንድ ይህ ስርዓት ይቀየርልን።

This petition had 426 supporters

The Decision Makers

office of the prime minster of ethiopia
office of the prime minster of ethiopia
Petition updates
Share this petition
Petition created on April 24, 2019