
ውድ ኢትዮጵያውያን መራጮች በአሜሪካ!!
የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በየከተማው ያሉ የአሜሪካ ምክርቤት እና ሴኔት ተወዳዳሪዎችን በምርጫ እንዲያልፉ እና ሀገራችንን የሚጠቅሙ ተወዳዳሪዎች እነማን ናቸው በሚል ስናናግር እና ስንከታተል ቆይተናል። በተለይም ካውንስላችን የአሜሪካን የምክርቤት ተወዳዳሪዎች የዲሞክራትም ሆነ የሪፐብሊካን በሚል እሳቤ ሳይሆን ከየተኛውም ፓርቲ የሆኑ ነገር ግን የኢትዮጵያን ጥቅም ሊያስከብሩ የሚችሉ እነማን ናቸው የሚለውን በጥልቀት ሲመለከት ነበር። በተለይም HR3600 ረቂቅ ህግን እና ተመሳሳይ መግለጫዎችን ሲሰጡ የነበሩ የፓርቲ አባላትን ባለመምረጥ በአንጻሩ ተፎካካሪዎቻቸውን በመደገፍ ጥቅማችንን ማስከበር ይኖርብናል በሚል የሚከተሉትን ደግፈናል። ኢትዮጵያውያን ከዚህ በሆላ በፓርቲ መስመር መምረጥ የለብንም መምረጥ ያለብን ማን ጥቅማችንን ያስከብራል የሚለውን ነው። ይህ ወደፊትም መቀጠል አለበት አለበለዚያ የአንድ ፓርቲ መራጮች ብቻ ሆነን ጥቅማችንን ማስክበር ይከብዳል። በሀገራችን ላይማእቀብ እና የተለያዩ ጭናዎች በሚፈጠርበት ሰአት ቁጣችንን ከዲፕሎማሲው ዘመቻ ውጪ የምናሳየው እንዲህ አይነት ምርጫ ሲመጣ በድምጻችን በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊ መራጭ ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት በፓርቲ ሳይሆን ጥቅማችንን በሚያስከብርልን የየትኛውም ፓርቲ ተወዳዳሪን በመደገፍ ወገንተኝነታችንን ለህዝባችን ማሳየት አለብን በመሆኑም የሚቀጠለው ሳምንት ምርጫ ኖቭምበር 8 ይህንን እያሰላችሁ ወደ የምርጫ ጣቢያው በመሄድ ድምጽ ለኢትዮጵያ ወዳጅ ለሆኑ ይስጡ!!
ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካወንስል