Mise à jour sur la pétitionPetition for formal investigation of Ejigayehu Kidane (Gigi Kiya) for hate crimes.Translation of the Petition in Amharic.
Bridges EthiopiaBrussels, Belgique
9 oct. 2018

Dear Friends,

Some have requested an Amharic translation of the petition and hence we provide it here.  Please pass along, share and pass it along to those who have not signed.  For those who are 18 years and older and agree with this message but are not computer savy, help them open an email account.  Assist them in adding their name to this petition.

ዘመኑ ጀርመን ለመቻቻል ፈር ቀዳጅ፤ለስብአዊ መብት ጠባቂና የቀድሞ በደልንም በማረም ረገድ መሪ ሆና የምትታይበት ነዉ፡፡የአንጌላ ሜርክል አስተዳደር በ2017 ለአንድ ሚሊዮን ጎስቁዋላ ሶሪያዉያን ስደተኞች ድምበሩዋን ክፍት ስታደርግ አለም ተደንቆአል፡፡ እናም የስደተኛ ማህበረሰቦች ንቁ የጀርመን ህብረተሰብ አካል በመፍጠር ለጀርመን የዳበረ ኤኮኖሚ እያደር የጀርባ አጥንት እየሆኑ ነዉ፡፡

ሆኖም አንዳንድ ግለሰቦች የጀርመንን የዜግነት መብቶችና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ህጋዊ ጥበቃ ሽፋን በተለያዩ ስፍራዎች ሰብአዊ መብቶችን የሚያስጠብቁ ተቁዋማትን ለማቁዋቁዋም በሚታገሉ ግለሰብና ቡድኖች ላይ የዘር ጥላቻን ለመቀስቀስ እየተጠቀሙበት ነዉ፡፡ የጀርመን ዜግነት ያላትና በሌቨርኩሰን ከተማ ነዋሪ የሆነችዉ ትዉልደ ኢትዮጵያዊት ወይዘሮ እጅጋየሁ ኪዳኔ ከእነኚህ ክፉኛ አሳሳቢ ከሆኑ ግለሰቦች መካከል አንዱዋ ነች፡፡ራሱዋን እንደኦሮሞ በማየት በስፋት በምትጠቀምበት ሶሻል ሚዲያና ዩቲዩብ ጥላቻን የሚያነሳሳና በበርካታ ነገዶች መካከል ጠላትነት እንዲፈጠር አድርጋለች፡፡የጀርመንን የዜጎች መብት ጥበቃ መጠጊያ በማድረግ ወይዘሮ ኪዳኔ ፍጹም ጸያፍ የሆኑ ድርጊቶችን ፈጽማለች፡፡ከዚህ በታች በተመለከቱ እጅጉን ተንኩዋሽ የሆኑ ቪዲዮዎቹዋ፤እንደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ባሉ ከተሞች የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎችን በቆንጨራ ሊጨፈጨፉ የሚገባቸዉ ወራሪና ሰርጎገቦች እንደሆኑ አድርጋ በመሳል ቀስቅሳለች፡፡ወይዘሪት ኪዳኔ ካሉዋት ከ100ሺ በላይ የፊስ ቡክ ተከታዮችና የጎላ የሶሻል ሚዲያ ሚና አንጻር በሴፕቴምበር 16፤2018 በቡራዩ ከደረሰዉ ከ50 በላይ ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎች በሚስማሮች፤ቆንጨራና መጥረቢያዎች ተጨፍጭፈዉ ከሞቱበት የዘር ማጥፋት ወንጀል ጀርባ አስተዋጽኦ ካላቸዉ ድርጊቶች አንዱ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ከነኚህ ቪዲዮዎችን መካከል ፤ግልጽ የሆነ የግድያ አፈጻጸም መመሪያና ‘’ሰፋሪ ‘’ያለቻቸዉን ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎች ስለማስወገድ መመሪያ የሰጠችባቸዉን ሁለት ትልልቅ ማሳያዎች ፤

https://m.youtube.com/watch?v=Kstumpp7rzk

https://m.youtube.com/watch?v=ah1Frsm2IIw

እኛ ፤ጥቂቶቻችንም የጀርመን ዜጎች የሆንን ከዚህ በታች የፈረምን ሰዎች፤የጀርመን መንግስት ወይዘሪት ኪዳኔን በጀርመን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ በቮክስቬርሄትዙንግ አንቀጽ መሰረት እንዲመረምራት እንለምናለን፡፡ እኤአ ከ1945-46 የዋሉት ኑረምበርግ ችሎቶች እንዳረጋገጡት፤ጀርመን የዘር ማጥፋት ወንጀል አነሳሾችንና ተጠያቂዎችን የማደን ተጨባጭ ታሪክ አላት፡፡በመሆኑም፤ እኛ ፈራሚወች ወይዘሪት ኪዳኔን ኢትዮጵያን እያዳረሰ ላለዉ የዘዉጌ ብጥብጥ ወይዘሪት ኪዳኔን ተጠያቂ በማድረግ ግለሰቡዋ ላይ ብርቱ ምርመራ እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡

ከቅርቡ የጀርመን ታሪክ ጫና አንጻር መላዉ የጀርመን ዜጋ በህግ የበላይነት ስር የመሆን ግዴታ አለበት፡፡ጀርመን ወደአገር ዉስጥ የፈለሱትን ፤ከለላ ጠያቂዎችንና ስደተኞችን የመቀበል የዳበረ ታሪክ አላት፡፡ጀርመንን እንደመኖሪያ ያደረገ ማንኛዉም ዜጋ በነኚህ ህጎች ስር የመኖርና ለብሄራዊ ስነምግባር፤ወንድማማችነት፤መግባባትና ታጋሽነት የራሱን አስተዋጽኦ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ስለሆነም፤ራሱዋ እንደ ፈላሲ በጀርመን ፈላሲያን ፖሊሲ ተጠቃሚ በመሆን በአገሪቱ የከለላ አሰጣጥ ህግ ስር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለ የዘር ማጥፋት ወንጀል ዉስጥ ሚናዋን በመጫወት ለቀጠለችዉ ወይዘሪት ኪዳኔናመሰል የጥላቻ ሰባኪያን ጀርመን እንደ ምቹ መደበቂያ እንዳትሆን እንጠይቃለን፡፡

የእናንተዉ፤

Bridges Ethiopia

Copier le lien
Facebook
WhatsApp
X
E-mail