📌የፕላስቲክ ቄጤማ ተከለከለ!
የፕላስቲክ ቄጤማ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከተከለከሉት የፕላስቲክ ምርቶች ውስጥ እንደሚካተት ተገለጸ
በሀገሪቱ እየተተገበረ ባለው የፕላስቲክ አጠቃቀም ክልከላ መሠረት የፕላስቲክ ቄጤማ ማምረትና መሸጥ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።
የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ፣ በተፈጥሯዊው ሳር (ቄጤማ) ምትክ እየቀረበ ያለው የፕላስቲክ ምርት በአካባቢና በጤና ላይ ከፍተኛ ብክለት እያስከተለ በመሆኑ ለመጠቀም ከተከለከሉት የፕላስቲክ ምርቶች ውስጥ እንደሚመደብ አብራርተዋል።
“ምርቱ አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል (Recycle) የማይመች በመሆኑ በቀጥታ አካባቢን ይበክላል” ያሉት ኃላፊው፡- ምርቱ በሀገር ውስጥ የሚመረት ከሆነ እንዲቆም፣ ከውጭ የሚገባ ከሆነም ሊታገድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም “እኛ የምናውቀውና የለመድነው ሕይወት ያለውን አረንጓዴ የተፈጥሮ ቄጤማ እንጂ ፕላስቲክ አይደለም” ብለዋል።
ስራ አስኪያጁ አቶ ዲዳ ማብራሪያቸውን ሲቀጥሉ፤ በክልከላው የተካተቱት ሁሉም ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶች መሆናቸውን ጠቅሰው የምርቱ ውፍረት እና መሰል መመዘኛዎች ከግምት ውስጥ እንደማይገቡ ተገልጿል።
የክልከላቸው ዋናው መስፈርት ምርቱ መልሶ ጥቅም ላይ የመዋል ዕድሉና ለአካባቢ በመበከል የሚኖረው አስተዋጽኦ ነው ተብሏል።
ፋብሪካዎች የማምረቻ ማሽኖቻቸውን በማዘመን ለአካባቢ ተስማሚ ወደሆኑ ምርቶች እንዲሸጋገሩ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ ይህም እንደ ሥጋት ሳይሆን እንደ አዲስ የሥራ ዕድል ሊታይ እንደሚገባ ተመላክቷል።
©️አሐዱ ሬድዮ
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
