Mental Health Hotline in Ethiopia የአእምሮ ጤና የድጋፍ አገልግሎት የሚሠጥ ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል መቋቋም

Petition Closed

This petition had 2,867 supporters

The Issue

Ethiopia has made strides in making robust mental health resources available and accessible to those who need it most. However, the gap between need and service is high and various barriers continue to hinder the delivery of quality mental health care to the general population. Many individual and collective efforts are required to address the complex needs of the mental health sector in the country. Establishing a toll-free mental health hotline will provide:

1. access to well-trained staff that can help provide accurate information and identify best resource options to address individual concerns

2. a primary pathway to direct those who can access care to the appropriate center or facility

3. an urgent touch point to defuse potentially life-threatening situations

Several steps have been taken to make a national mental health hotline a reality. Over the past few days, a social media campaign with the tag #Hotline4ET has gained traction. To help ensure that this continues to be at the forefront of the conversation, we have started this petition to collect signatures from those who support this initiative. If you believe the time to establish a national mental health hotline is now, please sign the petition today. We hope these signatures highlight to the Ethiopian Ministry of Health and other stakeholders the need to prioritize this effort.

If you have experienced mental health struggles or know someone who has, please show your support for this initiative by signing and sharing among your network. #Hotline4ET

ኢትዮጵያ በሀገር ደረጃ ጠንካራ የሆነ የአእምሮ ጤና ድጋፍ አገልግሎት ለማቅረብ እና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ የተለያየ ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ ነገር ግን እገዛ በሚፈልጉ ግለሰቦች እና በሚሰጠዉ አገልግሎት መሀል ባለዉ አለመጣጣም እንዲሁም በሚያጋጥሙ የተለያዩ ተግዳሮቶች ሳቢያ ደረጃዉን የጠበቀ የአእምሮ ጤና እንክብካቤ አገልግሎትን ለሠፊዉ ህብረተሠብ ተደራሽ እንዳይሆን እንቅፋት እየሆኑ ይገኛል፡፡ የሀገራችንን የአእምሮ ጤና ዘርፍ የተሻለ ለማድረግ በግልም እንዲሁም የተለያዩ አካላትን ርብርብ ይጠይቃል፡፡

የአእምሮ ጤና የድጋፍ አገልግሎት የሚሠጥ ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል መቋቋም ከሚሠጣቸዉ ጥቅሞች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡-

1. ግለሰቦች ለሚገጥሟቸዉ የአእምሮ ጤና እክሎች ትክክለኛ መረጃ እና ያሏቸዉን አማራጮች በባለሙያ የታገዘ ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

2. ድጋፍ የሚያስፈልጋቸዉን ግለሰቦች ወደሚመለከተዉ የጤና ተቋም እንዲያመሩ መነሻ ይሆናቸዋል፡፡

3. በህይወት ላይ አደጋ ከሚጥል ክስተት ሊታደግ ይችላል፡፡

ሀገር አቀፍ የአእምሮ ጤና የድጋፍ አገልግሎት የሚሠጥ ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል ለማቋቋም የተለያዩ ሙከራዎች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ጥቂት ቀናትም ይህንኑ እንቅስቃሴ የሚደግፍ #Hotline4ET የተሰኘ ንቅናቄ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ይህንን እንቅስቃሴ ለማገዝም የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፊርማ የሚጠይቅ የበይነመረብ ዘመቻ ይፋ ተደርጓል፡፡ ይህ የድጋፍ ማሰባሰብ የጤና ሚንስቴርን ጨምሮ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጥረታችንን ልዩ ትኩረት እንዲሰጡት ጉልህ ማሳያ ይሆናል፡፡ ስለሆነም የአእምሮ ጤና የድጋፍ አገልግሎት የሚሠጥ ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል ማቋቋምን የሚደግፉ ከሆነ እባክዎን በተዘጋጀዉ ማስፈንጠሪያ በመግባት የድጋፍ ፊርማዎን ያኑሩ፡፡

 

The Decision Makers

Ministry of Health - Ethiopia
Ethio Telecom

Petition Updates