

ሰበር ዜና Breaking News
ከረጅም ሂደት በሆላ በእርሰዎት ድጋፍና ትብብር የኢትዮጵያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል እና የኢትዮጵያን አድቮከሲ ኔትወርክ ዲያስፖራውን በማሰባሰብ አባይን ግድብ ጨምሮ #በዲፕሎማሲው መስክ ሀገራችን የተጀመረባትን #የሀሰት_ፕሮፖጋንዳ ለማክሸፍ፣ እንዲሁም ያሉ የሀገራችንን #እውነቶችን_ለአለም_ለማሳወቅ እና በሀገር ውስጥ ደግሞ የሀገራችንን ፖለቲካዊ ሂደት የተሳካ እና ፍትሃዊ የዲሞክራሲና ሰብአዊ መብት መከበር እንዲረጋገጥ ከአሜሪካን የምክር ቤት አባላትና የሚዲያ ኔትዎርኮች ጋር መስራት ያስችለን ዘንድ እንሆ በአሜሪካን ታዋቂ ከሆኑት ሶስት የተለያዩ ድርጅቶች የሎቢ እና የህዝብ ግንኙነት ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር እሮብ_አፕሪል_21, 2021 ዝግጅታችን ጨርሰን ለመፈራረም ተስማምተናል።
ይህ ሂደት እንዲሳካ አሻራችሁን በማስቀመጣችሁ ከ$165ሺ ዶላር በላይ ሰብስበናል። ታዲያ ገንዘብ በማዋጣት እና ምክር በመለገስ ለተሳተፋችሁ፣ ለረዳችሁ ውድ የሀገራችን የቁርጥ ቀን ልጆች ከልብ እናመሰግናለን።
ይህም በውጪ ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ በዲያስፖራ ታሪክ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ጉዳይ በራሳቸው ትብብር የቀጠሩት የሎቢና የህዝብ ግንኙነት የተግባር ስራ ሆኖ ይመዘገባል።
በዚህ ታሪክ የእርሰዎ አሻራ መኖሩን ሁሌም አይዘንጉ!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተክበራ ሁሌም ትኖራለች!!!
ያለውን ሂደት እንዲህ እየተከታተልን እናቀርባለን ፌስቡክ ፔጃችን ይከታተሉን።
https://www.facebook.com/EthiopianAmericanCivicCouncil/
Ethiopian American Civic Council & Ethiopian Advocacy Network.
አሻራዎትን ካላስቀመጡ አሁንም ጊዜ አለዎት እና የታሪኩ ተካፋይ ይሁኑ! Please click here.