አዛውንቱ ታዲዮስ ታንቱ በምህረት ይፈቱ!

9

Let’s get to 10 signatures!
Petitions with 1,000+ supporters are 5x more likely to win!

The Issue

አዛውንቱ ታዲዮስ ታንቱ በምህረት እንዲፈቱልን አቤቱታ፣

ምህረት የህግ ሥስ ልብ ነው::  ሁኔታንና ምክንያትን አመዛዝኖ ምህረት የሚያደርግ አካል የተከፋ ስሜቱንና የሚጨክኑ እጆቹን ያለዝብለታል:: በዚህም ከደረሰው በደል ተጨማሪ ሌላ በደል ላለመፈፀም ራስን ከማቀቡ በላይ ለኅብረተሰቡ ግንዛቤም ተስፋንና አመኔታን ይሰጣል::  እነሆም ለኢትዮጵያ መንግሥት አቤት ማለት የምንፈልገው ጉዳይ በርእሱ እንደተጠቀሰው  በእድሜያቸው ሩጫቸውን የጨረሱትን አዛውንት ታዲዮስ ታንቱን መንግሥት በአስተያየትና  በምህረት ከእስር እንዲፈታቸው ነው:: ያለ ነገርና ያለጉዳይ በከንቱ ለእስር እንዳልበቁ መረዳት ይቻላል:: ይሁን እንጅ:- 
1) ከተከሰሱበት ጉዳይ ባሻገር በፀሃይ መጥለቂያቸው ዘምን ላይ ያሉና 'ልጣቸው የራሰና ጉድጓዳቸው የተማሰ' ስለሆነ ተፈጥሮ ግዳጇን ትከውን ዘንድ በመፍቀድ የስብእና ርህራሄ ማሳየት ስለሚያስፈልግ፣ 

2) የመንግሥትን መሃሪነት ለማስረዳትና በሕዝብ ዘንድ የቻይነትን ስሜት ለማሰረፅ፣ 

3) በመተራረምና በሃሳብ ልዩነት አብሮ መኖርንና ሀገር መገንባትን ለማስተማር፣    

4) ከሁሉም ባላነሰ ምክምያት ደግሞ እኒህ አባት ከእስር እንዲፈቱ የመፈለግ መንፈስን የሚወተውተው  ለበቀሉበት ኅብረተሰብ ያለን ክብርና ምናልናትም የተራዘመው የአዛውንቱ እሥራት  በህዳጣንነታቸው ምክንያት እንደ አንዳንዱ ጉልቤ ኅብረተሰብ አባላት ጭሮ ለመድፋት ባለመቻላቸው አቅመቢስነት የተፈፀመባቸው እንዳይመስላቸው ነው::  
ከላይ በተጠቀሱትና ተመሳሳይ ምክንያቶች የተነሳ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል እኒህ አዛውንት ከእስር እንዲለቀቁ እንማፀናለን:: ይህ ቀና መእክት የደረሳችሁ ሁሉ ይህን የአቤቱታ ፒቲሽን በመደገፍ  እንድትተባበሩ ከልብ የመነጨ ጥያቄ ቀርቧል:: 

Petition Updates

Share this petition

Petition created on November 1, 2025