Massacre, Persecution, and Displacement of Orthodox Christians in Shirka woreda

89

Let’s get to 100 signatures!
Petitions with 1,000+ supporters are 5x more likely to win!

The Issue

 

   መስከረም 2019ዓ.ም

ጉዳዩ፡- በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ ወረዳ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና አጥቢያ አድባራት ላይ እየደረሰ ያለውን እልቂትና ውድመት ማስቆምን፣ ለተፈናቃዮች ሰብአዊ ድጋፍና የጉዳት ካሣ መጠየቅን ይመለከታል፣

ከላይ ለመግለጥ እንደተሞከረው እኛ የወረዳው ተወላጆች ይህንን አቤቱታ ስናቀርብ በቅድሚያ በወላጆቻችንና ዘመዶቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይና ግፍ እየተባባሰ በመምጣቱና ይልቁንም የተረፉት ወገኖቻችንም የወደፊት ህልውና አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መገኘቱን በመግለጽ መፍትሔ እንዲገኝለት ለማሳሰብ ነው።
በተጠቀሰው አካባቢ ኦርቶዶክሳውያንን መርጦ በማጥቃት የራስን እምነት በኃይል ለመጫን እየተፈጸመ ስለለው የወንጀል ድርጊት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ልዩ ልዩ የዜና አውታሮች የተገለጸና ከማንም ያልተሰወረ ሆኖ ሳለ የፌደራል መንግሥትም ሆነ የአካባቢው የመንግሥት አካል ዘላቂ መፍትሔ በመስጠት ዜጎችን ለመታደግ ያልቻሉበት ምክንያት ግራ የሚያጋባ አሳዛኝ እንቆቅልሽ ሆኖብን ይገኛል።
በወረዳው ውስጥ ነዋሪ በነበሩ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ስለደረሰው እልቂትና ጉዳት ከሥፍራው በተሰባሰበ ተጨባጭ ማስረጃ የችግሩን ጥልቀት ለማመልከት ያህል እንደሚከተለው እናቀርባለን፡-
ሀ. ሰብአዊ ጉዳትን በሚመለከት
ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በግፍ የተገደሉና አስከሬናቸው ተገኝቶ የቀብር ሥርዓት የተፈጸመላቸው ወገኖች ቁጥር 170 ነው። (ይህ አኃዝ ተገደው የተሰወሩትንና ወደ ገደል የተጣሉትን አይጨምርም)።
ተገደው የተሰወሩና ሁኔታቸው ያልታወቀ ወገኖች ብዛት 31 ነው።
የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ክርስቲያናት ብዛት (በ13/12/2018 ዓ.ም. የተፈጸመውን ጨምሮ) 33 ነው።
የመኖሪያ አካባቢያቸውንና የእርሻ ይዞታቸውን ትተው የተሰደዱ ወገኖች ብዛት በአባ ወራ ከ3000 በላይ ነው።
በእገታ ምክንያት በድምሩ ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ ከፍለው የተለቀቁ ወገኖች ብዛት 165 ነው።
ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ብዛት ለጊዜው በውል አልታወቀም።
ለ. በተቋማትና ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳትን በሚመለከት
በ2018 ዓ.ም. ብቻ በሦስት የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት የተቃጠሉና የፈረሱ ቤቶች ብዛት 456 ሲሆን ይህም በገንዘብ ሲገመት ወደ 99 ሚሊዮን ብር የሚሆን ነው።
የወደሙና የተዘረፉ የቤት ቁሳቁሶች ግምት 26 ሚሊዮን ብር ያህል የሚሆን ነው።
የተዘረፉ የቤት እንስሳት ግምት 4 ሚሊዮን ብር የሚሆን ነው።
ከማሳ ወይም ከጎተራ የተዘረፈ ወይም የወደመ እህል ግምት በኩንታል 900 ያህል ይሆናል።
በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ 37 አድባራት ውስጥ አኖሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ላላንጮ አማኑኤልና ሰንጎ እግዚአብሔርአብ ተብለው የሚታወቁ ሦስት አብያተ ክርስቲያናት አጥራቸው ሳይቀር ሙሉ ለሙሉ እንዲፈራረስ ተደርጓል፤ የተቀሩት 23 ያህሉ ደግሞ በተፈጸመባቸው የንብረት ዝርፊያ ምክንያትና አማንያኑ በስጋት መኖሪያ አካባቢያቸውን ትተው በመሰደዳቸው የተነሣ ተዘግተው አገልግሎት ያቋረጡ ሲሆን በከተማ አቅራቢያ የሚገኙ 11 ያህል አድባራት ብቻ ለጊዜው ያልተዘጉ ቢሆንም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የወደፊት ህልውና የሚፈታተን አደጋ መደቀኑን በመረዳት ልዩ ትኩረት እንድንሰጠው የሚያስገድድ ከባድ ስጋት ፈጥሮብናል፡፡
ከላይ በተጠቀሱት እንዲፈርሱ በተደረጉ ሦስት አብያተ ክርስቲያናት ሲገለገሉ የነበሩ በድምሩ 3487 ያህል ሰዎች ለስደት የተዳረጉ በመሆናቸው ሚታና ጋዶ፣ ሰንጎ ያያና ሶጂ ሳዴ የተባሉ ቀበሌዎች ሙሉ ለሙሉ ከክርስቲያናት እንዲጸዱ የተደረጉ ሲሆን በሌሎቹ 23 ያህል አጥቢያ የገጠር ቀበሌዎች ደግሞ ከ75/100 በላይ የሚገመቱ ኦርቶዶክሳውያንን የማጽዳት የተቀናጀ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።
አሁንም ቢሆን በወረዳው ውስጥ ባሉት ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ዘርፈ ብዙ ጥቃት ያላባራና በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ሆነው የዕለት ከዕለት ሕይወታቸውን በሰቀቀን እየኖሩ መገኘታቸው እረፍት የሚነሳ አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖብናል።
ስለዚህም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆናችሁ ብፁዓን አባቶቻችንና እንዲሁም የመንበረ ፓትርያርክ አስተዳደር ጉባኤ አባላት በሙሉ ጉዳዩን በቅርበት እንድትመረምሩና ከመንግሥት አካል ጋር በመነጋገር፡-
በታወጀባቸው አስከፊ ሞት ምክንያት በገዛ ሀገራቸው ስደተኛ ለሆኑት፣ በእገታና ከቤት ንብረት መፈናቀል ምክንያት በድህነትና ረሀብ ለተጎሳቆሉት፣ የሰላምን አየር ተነፍገው ብርቱ ኀዘንና ጭንቀት እያስተናገደም ቢሆን የአባትነት እስትንፋስና እቅፋችሁን በናፍቆት ለሚጠብቁ የመንፈስ ልጆቻችሁ የሚከተሉትን የመፍትሔ ሐሳቦች እንድታስፈጽሙልን በክርስቲያናዊ ፍጹም ትሕትና ራሳችንን ዝቅ በማድረግ በሰማዕታቱ ክቡር ደም ስም በብርቱ እንማጸናችኋለን።
ሀ/ ተፈናቃዮችን በሚመለከት
አፋጣኝ የቀለብና አልሚ ምግብ ድጋፍ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች እንጠይቃለን።
በስደት ለሚገኙ ተማሪዎች የመማርያ ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲመቻችላቸው እንጠይቃለን።
በየስርቻው ወድቀው በዝናብና ብርድ እየተንገላቱ ለሚገኙ ወገኖች መጠለያ እንዲመቻችላቸው እንጠይቃለን።
ከቤታቸውና የእርሻ ይዞታቸው የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ እርሻቸውና የመኖሪያ መንደራቸው ያለስጋት መመለስ እንዲችሉ የመንግሥት ጥበቃና ከለላ እንዲያገኙ እንዲደረግ እንጠይቃለን።
ለ/ የደረሰውን ጥፋት በሚመለከት
በዘረፋና እገታ ሰበብ ለተወሰደ ንብረትና ገንዘብ ካሣ እንዲከፈል ለሚመለከተው አካል ጥያቄ እንዲቀርብ እንጠይቃለን።
ለተቃጠሉ የመኖሪያ ቤቶችና አብያተ ክርስቲያናት ካሣ እንዲከፈል የሚመለከተው አካል እንዲጠየቅልን እንጠይቃለን።
ጥቃቱን በማቀድ፣ በማስተባበርና በማካሄድ የተሳተፉ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲጠየቅላቸው እንጠይቃለን።
ግድያ ለተፈጸመባቸው እንዲሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች የጉዳት ካሣ እንዲከፈል እንዲጠየቅላቸው እንጠይቃለን።
በግፍ የተገደሉት ወገኖች ቤተሰቦች ከፊሎቹ በስደት ላይ የሚገኙ በመሆናቸውና የቀሩትም ሀብት ንብረታቸውን ያጡ በመሆናቸው ጊዜውን ጠብቀው መታሰቢያቸውን ማድረግ እንደማይችሉ ታውቆ በቤተክርስቲያን እንዲታሰቡ እንዲደረግ እንጠይቃለን።
ሐ/ የጥቃት ስጋቶችን ለማስቀረት
ሃይማኖታዊ የበላይነትን ለመያዝ ጥቃት እየፈጸሙ ያሉ ኃይሎችን ድርጊት ከበቂ ማስረጃ ጋር ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲወገዙ እንዲደረግልን እንጠይቃለን።
ጥቃት እየተፈጸመባቸው ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ራሳቸውን የመከላከል መብት እንዲፈቀድላቸው እንዲደረግ እንጠይቃለን።
የጥቃት ስጋት ባላቸው አካባቢዎች የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ራሳቸውን ከጥቃት ለመጠበቅ እንዲደራጁ እገዛ እንዲደረግላቸው እንጠይቃለን።
ራሳቸውን ለመከላከል ለሚደራጁት ወገኖችም አስፈላጊው ቁሳዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው እንጠይቃለን።
በደረሰባቸው ጥቃት ምክንያት አካባቢያቸውን ትተው የተሰደዱ ወገኖችን መሬት ለሌላ የማስተላለፍ ድርጊት እንዲቆም ለሚመለከታቸው ማሳሰቢያ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።

የፈጠራ ትርክትና ሀሰተኛ ውንጀላን መሠረት አድርጎ በዛቻ፣ በዘረፋ፣ በእገታ፣ ንብረት በማውደምና አሰቃቂ ግድያ በመፈጸም ቤተክርስቲያንና ልጆቿን የማሳደድ ድርጊት እንዲቆም በሃይማኖት ተቋማት ኅብረት በኩል ጥረት እንዲደረግ እንጠይቃለን።
መ/ መንፈሳዊ አገልግሎትን በሚመለከት፦
በወረዳው ውስጥ ያሉና እንዲሁም የወረዳው ተወላጅ ሆነው በሌላ አካባቢ የሚኖሩ ታዋቂ ግለሰቦችን ያካተተ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት የሚያስችል የምክክርና እርቀ ሰላም ጉባኤ በገለልተኛ አካል እንዲዘጋጅ እንዲደረግ እንጠይቃለን።
ተደጋጋሚ ጥቃቶች እየተከሰቱ ባሉባቸው አካባቢዎችና አስጊ ቀጠናዎች ውስጥ ለሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እስኪያገኝ ድረስ ራሳቸውን ለክብረ ሰማዕት ሞት እንዲያዘጋጁ ተገቢ ትምህርት እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን።
በስጋት ቀጠናዎች ውስጥ የሚገኙ አማኞች ሁሉ እርስ በርሳቸው ያላቸውን ግጭት፣ ቂምና ጥላቻ አስወግደው በአንድነት ለመቆም የሚያስችላቸውን አቅም እንዲያገኙ እርቀ ሰላም እንዲያደርጉ መንፈሳዊ ጥሪ እንዲተላለፍላቸው እንጠይቃለን።
በስጋት ቀጠናዎች ውስጥ የሚገኙ አማኞች ሁሉ በእምነታቸው ጸንተው መቆም እንዲችሉ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ሕይወት በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ እንዲደረግ እንጠይቃለን።
በእምነታችን ላይ ያንዣበበብንን የጥፋት ዳመና በእግዚአብሔር ቸርነት ለማራቅ የንስሐና ጾም ጸሎት ጥሪ ለሁላችንም እንዲደረግና የምህላ ጊዜ እንዲታዘዝልን እንጠይቃለን።
ቤተሰቦቻቸውን በግድያ ምክንያት ላጡትና ከቤት ንብረታቸውም ለተፈናቀሉት ወገኖች የማጽናኛ መርሐግብር ተዘጋጅቶ እንዲጎበኙ እንዲደረግ እንጠይቃለን።
ሃይማኖታቸውን ተገድደው ስለቀየሩ ወገኖች ጉዳይም አስፈላጊው ማጣራት እንዲደረግ እንጠይቃለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
ግልባጭ
ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ ጽ/ቤት
ለኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት

 

 

 

 

Societies of Shirka woreda,East Arsi Diocese  
September ,2026 


To:  
The Office of the Holy Synod Ethiopian Orthodox Tewahedo Church  

The Patriarchate General Office Ethiopian Orthodox Tewahedo Church  
Addis Ababa, Ethiopia  

Subject: Petition Regarding Massacre, Persecution, and Displacement of Orthodox Christians in Shirka woreda

Your Holiness and Esteemed Fathers,  

We, the undersigned societies of Shirka woreda, respectfully submit this petition to bring to your immediate attention the grave atrocities being committed against Orthodox Christians in our district. The suffering of our people marked by massacres, forced displacements, abductions, and destruction of churches,homes has reached a critical level, threatening the survival of our community.  

Despite repeated reports by domestic and international outlets, neither federal nor local authorities have provided lasting protection or solutions. We therefore appeal to you, our spiritual fathers, to intervene and advocate on behalf of our Ortodox communities suffering.


To mention some of the evidence of atrocities:

A.Human Casualties and Impact  
- 170 individuals murdered since 2016 E.C.  
- 31 individuals forcefully disappeared, fate unknown  
- 33 Christians injured, including during the 13/12/2018 EC or August 19, 2026 attack  
- Over 3,000 households displaced from homes and farmlands  
- 165 abductees released after ransom payments totaling 35 million Birr  
- Numerous students forced to abandon education  

B.Damage to Institutions and Property:
 
- 456 houses burned in 2018 E.C., losses estimated at 99 million Birr  
- Household goods looted worth 26 million Birr; livestock worth 4 million Birr  
- 900 quintals of grain destroyed or looted  
- Three churches (Anole St. George, Lalincho Ammanuel, Sengo Egziabherab) demolished  
- 23 churches closed due to looting and displacement; only 11 remain open under threat  
- Entire kebeles (Mitana Gado, Sengo Yaya, Soji Sada) cleared of Christians  

Our Requests

A. For Displaced Persons  
- Immediate provision of food, shelter, and medical support  
- Educational assistance for displaced students  
- Security guarantees for safe return to homes and farmlands  

B. For Damages and Losses  
- Compensation for looted property, burned houses, and demolished churches  
- Justice for perpetrators of massacres and coordinated attacks  
- Support for families of the murdered and injured  
- Official commemoration of victims by the Church  

C. To End the Threat of Attacks  
- Expose and condemn forces imposing religious dominance  
- Guarantee the right of Orthodox Christians to self-defense  
- Provide material support for community protection  
- Halt illegal transfer of farmlands and properties of displaced Christians  
- Engage the Inter-Religious Council to stop persecution and displacement  

D. For Assured Spiritual Services  
- Organize impartial reconciliation forums with district leaders and diaspora natives  
- Provide spiritual education to strengthen faith and resilience  
- Issue pastoral calls for unity, repentance, fasting, and prayer  
- Decree a period of divine mercy (Mehela) to seek God’s grace  
- Establish pastoral comfort programs for bereaved and displaced families  
- Investigate forced conversions under duress  

Conclusion:  

We, your spiritual children, bow in humility and faith, imploring you to act swiftly on behalf of those who have been displaced, impoverished, and deprived of peace. May your fatherly guidance and intervention bring relief and hope to our community.  

May We Receive Your Blessing.  

Respectfully submitted


CC:  
Office of the Ethiopian Human Rights Council (EHRCO)  
Office of the Inter-Religious Council of Ethiopia (IRCE)  
Addis Ababa, Ethiopia

 


 

The Decision Makers

Ethiopian Holy Synod
Ethiopian Holy Synod
Addis Ababa

Petition Updates

Share this petition

Petition created on September 16, 2026