ሀሰተኛ አጥማቂያን እንቃወማለን

1,256

The Issue

በቴክሳስ ጠቅላይ ግዛት በዳላስ / ኧርቪንግ ከተማ ሊቋቋም ስለታሰበው "የጥምቀት አገልግሎት" መስጫ ቦታ ምስረታን በመቃወም የተዘጋጀ የፊርማ ማሰባሰቢያ ሰነድ!

....የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ ...  ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ !   ማር 4፤24

ይህ ቃል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶ በትምህርቶቹ መጨረሻ ላይ ለሚሰሙት ሁሉ  የሚነግራቸው ቃል ነው፤ በብዙ ቦታ ከማቴዎስ እስከ ዮሐንስ ራዕይ በወንጌላችን ላይ የምናገኘው ኃይለ ቃል ነው። ጌታችን በዚህ ስፍራ  “ የሚሰማ ጆሮ “ አለ እንጅ ‘ ጆሮ ያለው ይስማ ‘ ብቻ አላለም፤ ምክንያቱም ጆሮ ያለው ሁሉ እንደማይሰማ ሁሉን አዋቂ የሆነው ጌታ ያውቃልና።

የቤተ ክርስቲያን ማለትም የክርስቶስ የአካሉ ብልቶች ለሆናችሁ ሁሉ !

በዘመናችን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የተወደደ ሐዋርያ ጳውሎስ በ ሐዋ ሥራ 20:29 ላይ እንደነገረን  ለመንጋው የማይራሩ፤ ጨካኞች፤ ተኩላዎች ብሎ የገለጣቸው / ካህናት ሳይሆኑ ካህናት ነን በማለት / በየስርቻው መሽገው የዋህ የሆነውን አማኝ በህይወት ዘመን ውስጥ ከሚገጥም ልዩ ልዩ መከራዎች እንታደግሀለን በማለት፤ ከእግዚአብሔር ባልሆነና ልዩ በሆነ የመናፍስት አሰራር ሕይወቱን፤ ኑሮውን፤ ትዳሩን፤ የነገ ተስፋዎቼ የሚላቸውን ልጆቹን ሳይቀር በሚያሳዝን ሁኔታ እየተነጠቀና ለጨካኝ እየተሰጠ ይገኛል፤ እንዳለመታደል ሆኖ እንዲህ ካለው ጨካኝ የሚያስጥልና ነፍሱን ስለበጎቹ የሚያኖር እረኛ ቀርቶ ሥጋዊ ጥቅሙን እንኳን የሚተው ሙያተኛ በዚህ ዘመን አልተገኘም፤ ዮሐ 10፤11

ይህ በርቀት እየሰማን ልባችን የሚያዝንበት አሰራር ዛሬ በከተማችን በ DALLAS TX. ነገ ደግሞ በ HOUSTON TX. ሥሩን በመትከል በዝርዎት የሚገኘውን ህዝባችንን ለገንዘብ ጥቅም ሲል የመናፍስት ቁራኛ ለማድረግ መሰረቱን በመትከል ላይ  ይገኛል፤ሆኖም ይህ ጉዳይ ሳይቃጠል በቅጠል እንደሚባለው በሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ይሁንታ አግኝቶ በቤተክርስቲያናችን ስም ይህን የጥፋት መሰረት ከመጣሉ በፊት አደጋው የሚታየንና የሚያሳስበን ሁላችን በአንድነት ሆነን ከዚህ ማብራርያ ጋር በተያያዘው የፈርማ መዝገብ ላይ ስማችንን፤ የምንኖርበትን ከተማ፤ አጥቢያ ቤተክርስቲያናችንን፤ ስልክ ቁጥራችንን በማስቀመጥ  የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ ይህንን የጥፋት ተልዕኮ ቡራኬና እውቅና ባለመስጠት መንጋውን በቅዱስ ጴጥሮስ በኩል ጌታና መድኃኒት ከሆነን ከኢየሱስ ክርስቶስ ባገኙት ስልጣን ህዝባችንን እንዲታደጉልን እንጠይቃልን፤ ብሎም ለቤተክርስቲያናችን መንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት በግልባጭ እናሳውቃልን።

እናንት የክርስቶስ የአካሉ ብልቶች የሆናችሁ ሁሉ በዚህ አገልግሎት እንድትሳተፉና ይህንን የጥፋት መልዕክተኛ ተባብረን እንድናስቆመው ስንል የቤተክርስቲያን እረኛና መጋቢ በሆነው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስም እንማልዳችኋለን።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!

Supporter Voices

Petition Updates

Share this petition

Petition created on July 6, 2025