STOP FORCEFUL EVICTION OF AMHARAS

STOP FORCEFUL EVICTION OF AMHARAS

0 have signed. Let’s get to 25,000!
At 25,000 signatures, this petition becomes one of the top signed on Change.org!

Amhara Ethiopians started this petition to PRIME MINSTER ABIY AHIMED and

ባለፉት 27 ዓመታት አማራውን በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች መጨፍጨፍ፣ ማፈናቀልና ሀብት ንብረቱን መዝረፍ የተለመደ ሆኖ ቆይቷል፡፡ አልፎ አልፎ ችግሩ የቆመ ቢመስልም አሁንም እንደገና በአዲስ መልክ ተቀስቅሶ በርካታ አማሮች ተፈናቅለው ለጎዳና ተጋልጠዋል፤ ሕይወታቸውንም አጥተዋል፡፡

 በተለይ ደግሞ በቅርቡ የአማራ ተወላጆች የትኛውንም ያክል የቤተሰብ ቁጥር ቢኖራቸው ከ2 ሔክታር መሬት በላይ ማግኘት አይችሉም በማለት ለዘመናት ግብር ሲከፍሉበት የቆዩትን መሬታቸውን እየተቀሙ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በስፋት ተፈናቅለዋል እየተፈናቀሉም ነው፡፡ በምዕራብ ሸዋ፣ በምስራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ በጂማ፣ በቡኖ በደሌና በሌሎችም አካባቢዎች የተፈናቀሉ አማሮች በአዲስ አበባ፣ በባሕር ዳር፣ በቆቦና በወልዲያ አካባቢዎች በርካታ ሕጻናት፣ አዛውንቶችና አቅመ ደካሞችን ጨምሮ ጎዳና ላይ ፈሰው ይገኛሉ፡፡ በቤኒሻንጉል ከመተከልና ከማሽ ዞኖችም ከ10 በላይ ሰዎቸ ሲገደሉ ከ2000 በላይ ቤተሰቦች ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡ በደቡብ ከቤንች ማጂ ዞን በሚዛን፣ አማንና ቴፒ ከተሞች የአማራ ተወላጆች ንብረት በብዛት ወድሟል፡፡ በርካታ አማሮችም ታስረዋል፡፡ ሕጻናት ከትምህርታቸው ታግደዋል፤ አማሮች በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ የመሥራትና የመለወጥ መብት ተነፍጓቸዋል፡፡

 ይህ ጉዳይ በአስቸኳይ ካልቆመና ጥቃት ለሚደርስባቸው አማሮች አስተማማኝ ጥበቃ ካልተደረገላቸው የአገራችን አንድነት የከፋ አደጋ ላይ ከመውደቁም በላይ ወደእርስ በእርስ ብጥብጥ የሚያመራ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም በአዲሱ ጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር ዓቢይ አሕመድ የሚመራው መንግሥት በአማሮች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት እንዲያቆም /እንዲያስቆም ብሎም ድርጊቱን በሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን፡፡

0 have signed. Let’s get to 25,000!
At 25,000 signatures, this petition becomes one of the top signed on Change.org!