የአኖሌን የጥላቻ ሐውልት እንዲያፈርስ የኦሮሚያን ክልል መንግስት መክሰስ

የአኖሌን የጥላቻ ሐውልት እንዲያፈርስ የኦሮሚያን ክልል መንግስት መክሰስ

0 have signed. Let’s get to 100!
At 100 signatures, this petition is more likely to be featured in recommendations!
Wendemsesha Ayele Angelo started this petition to Attorny at law and

የኦሮሚያ ክልል መንግሥትን እንከሳለን!
የጥላቻው ሐውልት እንዲያፈርስ!
ጊዜው የሕግ ማስከበርም አይደል?
የኦሮሚያ ክልል መንግሥትም ለኢትዮጵያ አንድነትና ለሕዝብ ሰላም እሠራለሁ ብሎም የለ?
የጥላቻ ንግግሮችና ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ድርጊቶች እንዲቆሙ ይፈለግም የለ?
የተዛባ ታሪክ ትረካ ለጥላቻና ሰላም እጦት ምክንያት ይሆንም የለ?
ታሪክን ለመዘከር የሚያስፈልገው ሐውልት እውነትን መመስከር አለበትም አይደል?
የታሪክ ምሁራን ከየብሔረሰቡ እየቀረቡ እውነትን ማስረዳት ይችሉም የለ?!
……
ታዲያ ምን ያጣላናል?
እውነቱን ፍርድቤት ይፍረድልና፤
ምስክር ሞልቶናልና፤
ተከሳሹ የኦሮሚያ ክልል መንግሥትም ለሠራው ሐውልት ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበትና፤
የኦሮሚያ ክልል መንግሥትም ካልበቃ ሌላ ወገን ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር መብት ስላለው የጃ-ዎርም ሆነ ሌላ ቡድን ቀርቦ እንዲከራከር መብት አለውና፤
የፍርድቤት ውሳኔም ላይ ቅሬታ ያለው እስከሰበር ሰሚ ድረስ ቀርቦ መከራከር መብቱ ነውና፤
የፍርድቤት የመጨረሻ ውሳኔን የማስፈጸም ግዴታ የተሸናፊውና የመንግሥት ሥራ ነውና፤
……
የክሱ ጭብጥ!
የአኖሌን የጥላቻ ሐውልት በመገንባቱ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ሕዝብን በሕዝብ ላይ በጥላቻ በማነሳሳት ጥፋተኛ ተብሎ እንዲወሰነልን፤
ሐውልቱን ውሳኔው በተሰጠ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያፈርስ፤
የሕዝብን/ብሔረሰቦችን መቀራረብና መግባባት የሚያጠናክር ሐውልት በኦሮሚያ ክልል ዋና ዋና ከተሞች እንዲገነባ፤
በዚህም ምክንያት ለተፈጠሩ ችግሮችና ጉዳቶች ይቅርታ እንዲጠይቅ፤
በሐውልቱ ምክንያት የተፈጠረውን የጥላቻ አመለካከት ሊያጠፋ የሚችል ቅስቀሳና ትምህርት ሥራ ለቀጣይ 5 ዓመታት በኦሮምኛ ቋንቋ እንዲያካሂድና ለፍርድቤትና ለሕዝብ በየወሩ ሪፖርት እንዲያቀርብ፤
የዚህን ፍርድ ውሳኔ አፈጻጸም በየ6 ወሩ ለሚዲያዎች ሁሉ በኦሮምኛና በአማርኛ መግለጫ እንዲሰጥ፤
ጠቅላላ የ5ቱን ዓመት አፈጻጸም ለፍርድቤት እንዲያቀርብና ከሳሽ ቀርቦ መስክሮ መዝገቡ ለመጨረሻ ጊዜ እንዲዘጋ ወይም የጎደለ ካለ እንዲታይ፤
ይህን የምትደግፉ በፊርማችሁ አረጋግጡና ክሱን ወደፍርድቤት እንወስደዋለን፡፡
Share

0 have signed. Let’s get to 100!
At 100 signatures, this petition is more likely to be featured in recommendations!