ፍትሕ ለዐማራ ሕዝብ! Justice for Amara!

0 have signed. Let’s get to 200!


 ፍትሕ ለዐማራ ሕዝብ፤

ባለፉት 28 ዓመታት በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ፖለቲካ የፈላጭ ቆራጭነቱን ቦታ የያዘው የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ፣ ዐማራውን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ፣ ከ5,000,000 (ከአምስት ሚሊዮን) በላይ ዐማራ ከምድረ-ገጽ እንዲጠፋ ማድረጉን የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዐማሮች ሀብት ንብረታቸውን ተነጥቀው እንዲፈናቀሉና አገር የለሽ እንዲሆኑ ተደርጓል። የዐማራውን ነገድ በቁጥር አናሳ ለማድረግ በወሊድ መቆጣጠሪያ ስም ወላድ የዐማራው ሴቶችን አምካኝ እንክብልና መርፌ በመስጠት፣ዐማራው ተከታይ ትውልድ እንዳይኖረው ተደርጓል። በትምህርት ከሌሎች ክልሎች የደከመ እንዲሆን ሆን ተብሎ ዐማራው እንዳንይማር የተለያዩ መሰናክሎች ተጥሎበት የበይ ተመልካች ተደርጓል። ጤንነቱ የታወከ እና በቀላሉ ሊፈወሱ በሚችሉ ተላላፊ በሽታዎች እንዲጠቃ ነባር ተቋማቱን በማፍረስ ታማሚና ሟች እንዲሆን ተደርጓል።

ከሁሉም በላይ ዐማራው ባለፈ ታሪኩ እንዳይመካ፣ በአንፃሩ ወጣቱ ያማራ ልጅ በአባቶቹ ማንነትና ተግባር ተሸማቃቂ እንዲሆን፣«ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛ፣ አድኃሪ፣ በዝባዥ፣ ጨቋን ብሔርና ገዥ መደብ» የሚሉ ቅጽሎችን በመለጠፍ ትውልዱ የሥነልቦና ተጠቂ እና ተሸማቃቂ ለማድረግ ብዙ እርቀት የተሻገረ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ተሰርቶበታል። በትግሬ-ወያኔው ሕገመንግሥት የዜግነት መብት የሌለው ከመሆኑም በላይ፣ ዐማራው በተለይ በኢትዮጵያ ግዛት የመኖር መብቱን የገፈፈ በመሆኑ፣ ዐማራው አገር አልባ ሆኗል። በዚህም የተነሳ በተገኘበት የሚሳደድና ንብረቱን የሚቀማ ሆኗል።

እነዚህና መሰል ድርጊቶች ሲጠቃለሉ በዐማራው ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስለዘር ማጥፋትና ዘር ማጽዳት ወንጀሎች ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟላ እንደሆነ የሕግ ሙያተኞች ይስማማሉ። ይህ በዓለም አቀፍ ድንጋጌ የተወገዘና፣ ከወንጀሎች ሁሉ ወንጀል ሆኖ በዓለም አቀፍ ሕግ የሚያስጠይቅ እንደሆነ የሚታመንበት ወንጀል በዐማራው ላይ የተፈመፈጸመ ስለሆነ፣ ይህ ወንጀል የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን፣ልዩ መርማሪ አካል አቋቁሞ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ እንዲቻል ፣ በዐማራው ላይ የተፈጸሙትን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች ዝርዝር፣ ከከፍተኛ ቁጥር ፊርማ ጋር ለኮሚሽኑ ማቅረብ፣ ኮሚሽኑ ሊወስድ ስለሚገባው ሕጋዊ አግባብ መነሻ ሊሆን እንደሚችል ስለታመነ፣ መረጃዎችን ከማሰባሰብ ጎን፣ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ  አስፈላጊ ሆኗል።

ስለሆነም በሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅትና በዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ትብብር«ፍትሕ ለዐማራ» የተሰኘ ግብረ-ኃይል ተመሥርቶ መረጃዎችን በማሰባሰብና በማጠናቀር ላይ ይገኛል። ግብረኃይሉ የሰነድ፣ የቃል፣ የምስል፣ የቦታና መሰል መረጃዎችን አስባስቦ ለሕግ አግባብ በሚያመች መልኩ እያቀናበረ ይገኛል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ፣ቢያንስ በዐማራው ላይ ለተፈጸመው የዘር ጥቃት፣ ወንጀለኞቹ ለፍርድ ይቅረቡ የሚሉ ከ50,000 ያላነሰ ፊርማ አሰባስቦ ለኮሚሽኑ ማቅረብ ሂደቱን እንደሚያፋጥነው ታምኖበታል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ፣ይህን የፊርማ ማሰባሰቢያ ሰነድ አዘጋጅቷል። ለሰብአዊ መብት መከበር የቆሙ፣ ከሁሉም በላይ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው የዐማራው ነገድ ተወላጆች ሰነዱን በመሙላትና በማስሞላት እንዲተባበሩን ጥሪአችን በአክብሮት እንቀርባለን።

ፍትሕ ለዐማራ!

ፍትሕ ፍትሕን ላጡ ሁሉ!  

 Today: Tekle is counting on you

Tekle Yishaw needs your help with “ASEU: ፍትሕ ለዐማራ ሕዝብ!!”. Join Tekle and 169 supporters today.