FREE ETHIOPIAN PRISONERS OF WAR IN ERITREA

0 have signed. Let’s get to 200!


የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስደት መንግስት (Ethiopian National Government In Exile) USA.
       

 ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሊ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ፡ አፍሪካ።

በመጀመሪያ የከበረ የኢትዮጵያዊትነት ስለማታዬ ይድረስህ።

Free Col. Bezabh Petiros, 

Col. Bezabh Petros, Ethiopian Air Force pilot, has been POW, (captured at the Badme War) in1998. 

ባድመን አስመልክቶ ከኤርትራ ጋር ኢትዮጵያ የምታደርገው ስምምነት ፡ የኢትዮጵያን ሙርከኞች ያስቀደመ መሆን ይገባዋል። ይሄውም ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን የባድመው ጦርነት ሰለባ የሆነውን መጨመር አለበት። በሕይወት ይኖር አይኑር ቤተሰቡ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ አለበት። በተያዘበት ጊዜ ምን አደጋ አልደረሰበትም ነበር ቲንሽ ክንዱን ከመጎዳት ሌላ ስለዚህ ያኔ አለመሞቱን ልገልጽልህ እወዳለሁ።

ስለሆነም የኢትዮጵያን ሙርከኞች አስለቅቀህ በኢትዮጵያ አይር መንገድ ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ይዘሃቸው እንድትመለስ በትህትና አሳስባለሁ። ሏኡካን ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ በሚል ካንተ ስሰማ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባስተላለፍከው መሰረት ፡ የሉኡካኑም አባላት እነማን መሆናቸውን አስመራ ባለኝ ግንኙነት ጠይቄ እንደተረዳሁኝ ፡ ከባድመ ጉዳይ ጋር አያይዘህ የሙርከኞቹን መረከብ ጉዳይ እንድታቀርብ አስቸኳይ ደብዳቤ ጽፌልህ ነበር። ስለሙርከኞቹ ቀድሞም እንዳልተነሳ ስለተረዳሁኝ በፐቲሽን መልክ ማቅረቡ ባስቸኳይ ምናልባትም በአንድ ሰአት ውስጥ ፐቲሺኑ ይፋ እንደተደረገ ስለሚደርስህ እስከዛሬ ድረስ መንግስት ባጣው ሙርከኛ ስም እናም ወገን የለህ መለዮለባሽ ስም በፐቲሽን መልክ ጉዳያቸውን አስመልክቶ ላሳስብህ ተገድጃለሁ።

እንድታውቀው ያህል ፡ በበኩሌ መለስ ዜናዊ ሙርከኞች የሉኝም ብሎ መልስ ሲሰጠኝ ለዩኤስ እና ለዩኤን ጭምር
መጀመርያ እየሱስ ክርስቶስ እሱ መድሃኒዓለም ባዘዘው መሰረት ሙርከኞቹን ጀግኖች ለማስለቀቅ የዜግነት ግዴታዬን ተወጥቻለሁ። የመጀመርያውንም የሰላም ጥሪ እና የጦርነት አቁሙ ጥያቄ ለፕሬዘደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በ1999 በግሪጎሪያን አቆጣጠር በአስመራው ተቀብሎ ባነጋገረኝ ጊዜ ከአንድ ሰዓት ተኩል የበለጠ የሃሳብ መለዋወጫ ስብሰባችን ላይ እንዳቀረብኩለት እና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት አሰብም ለኢትዮጵያ እንድትመለስ ጭምር ማሳሰቤ የማይካድ እና በጊዜው ጀግናው የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እናም የአለም አቀፉ ሚዲያ በሰፊው የመዘገቡት መረጃ ምስክር ነው። ሕዝብ ለሕዝብ ለማስታረቅ ፡ ቁስል ማዳን የሰላም የመጀመርያው ጥንሥስ በመሆኑ ፡ የመጀመርያውን ዘላቂ የሰላም እና የእርቅ ጥሪ በኢትዮጵያ ሕዝብ እና በኤርትራ ሕዝብ ማሃል ሰላም ለማስፈን ሁለተኛውን ጦርነት በባድመ ሊጀመር መለስ እየተዘጋጀ በነበረበት ጊዜ ነበረ ፡ ከሕዝቡ መሃል ከተውጣቱ ኤርትራውያን በተለየም ኢትዮጵያዊነን እያሉ በመለስ ዜናዊ በክህደት ያባረራቸው የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ጭምር በሱማሌም ሐረርን ከሱማሌ ያስለቀቁ ወታደሮችን ጭምር ያካተተ ፡ የኤርትራን መንግስት ወክሎ ስብሰባውን ከእኔ ጋር ያስተባበረው ፡ አምባሳደር ተስፋማሪያም ተከስተ። ስብሰባውም የተደረገው በሰንሻይን ሆቴል አዳራሽ ውስጥ ነበር። ይሄ በ1999 ኦክቶበር ውስጥ ከኤርትራ መንግስት እና ከሕዝቡ ጋር የተጀመረው የሰላም ጥሪ ጅምር ከዛ ኋላ ለመጡት መነሻ እና በር ከፋች ሆኖ ቆይቷል።

የትጋርይን ተራራ እንዲያለሙ በሙርኮ በባርነት ትግራይን ያለሙ
ሌላው ፡ በ1991 በኤርትራ የሙርኮ ሰለባ ከሆኑት ግማሾቹ ወደ አዴግራት ተወስደው በመለስ ትእዛዝ የትግራይን ተራራ አልምተው ጫካ ያደረጉትንም እዛው ትግራይ በሕይወት የተረፉት ታስረው እና እያገለገሉም ስላሉ የእነሱንም ነጻነት በዚህ አጋጣሚ እጠይቅሃለሁ። ጊዜው አሁን ነው ባንተ በኩል ከኤርትራም ከትግራይም ሙርከኛውን በሙሉ ነጻ የማውጣቱ ጉዳይ።

ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ሙርከኛ ያልነበሩ ሆኑም ነገር ግን ታስረው ከወር በፊት ያስለቀኳቸውን አስመልክቶ ማለትም ፡ ከብዙ ሚስጥራዊ ጥረት በኋላ እዛው አስመራ ስለሚገኙ ፡ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህን እኝህን የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ አይር ኃይልን ጀግና ፡ ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ይዘሃቸው በመግባት ከዛም ወደ ውጪ ለሕክምና እንዲሄዱ ታደርግ ዘንድ እጠይቃለሁ።

መረሳት የሌለበት እያንዳንዱ ሙርከኛ ፡ ልጆች ፡ ሚስቶች ፡ ዘመዶች ፡ ጓደኞች እንዳለው እና የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እስከዛሬ እየጠየቀው ያለ ትልቅ አንገብጋቤ ጉዳይ ስለሆነ ጥያቄዬ ቶሎ መልስ ባነትበኩል ያገኛል ብዬ በእኔም በድርጅቴም ስም አሳስብሃለሁ።

የሐረርወርቅ (የኢትዮጵያወርቅ) ጋሻው።
ሊቀመንበር እና መስራች።

For your information , Yeharerwerk Gashaw, Ethiopian Prisoners of War        freedom Advocate in Eritrea with the POWS (1999).

1.Eritrea https://www.youtube.com/watch?v=FnWfamb843M&t=150s

2.https://www.youtube.com/watch?v=HsSdHIw2ms8

3.https://www.youtube.com/watch?v=XCm89nXDS2w

4.://www.youtube.com/watch?v=Aoai0SlnUQY

 5.https://www.youtube.com/watch?v=xXGUNfeasNg&t=1225s

6. Ethiopian National Government In Exile (ENGIE) press release, http://welkait.com/?p=15366

The freedom of Ethiopian POW and The unity and peace seed was planted between Ethiopian and Eritrean brothers and sisters in Asmara,1999 at Sunshine Hotel, by Yeharerwerk Gashaw.
The evidence speaks for itself.
Take a look at the peace talk.

ቁጥር አንድ የመጀመርያው የሰላም ምክክር ንግግር እና ጥሪ በአስመራ መረጃ https://www.youtube.com/watch?v=fNNIjgPg-Cc

ቁጥር ሁሉት የመጀመርያው የሰላም ምክክር ንግግር እና ጥሪ በአስመራ መረጃ፡
https://www.youtube.com/watch?v=d_R2PHAD14o

ልጆች የባድመ ጦርነት ላይ ለገሰ ዜናዊ (መለስ) አስጨርሶአቸው የተረፉት በሙርከኝነት ኤርትራ ውስጥ እናም ወታደሮች ሙርከኞች።
https://www.youtube.com/watch?v=FnWfamb843M

For more information, email: Yeharerwerk Gashaw at yehar9@aol.com