የካቲት 12 ሠላሳ ሺህ ኢትዮጵያውያን የተጨፈጨፉበት የሰማዕታትን ቀን የተወካዮች ምክር ቤት በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበር እንዲወስን ይፈርሙ።

0 have signed. Let’s get to 1,000!


የተወካዮች ምክር ቤት እንዲወስን ፊርማዎን እንዲያሳርፉ በሰማዕታቱ ስም ይለመናሉ።

ከየካቲት 12-15 /1929 ዓም አዲስ አበባ ከነዋሪዎችዋ ከሠላሳ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ በጨካኝ ፋሺሽት ወታደሮች እና ግብረ አበሮቻቸው ተጨፍጭፈዋል።በዓሉ ላለፉት አርባ ዓመታት በተለየ ደግሞ ላለፉት ሀያ ስምንት ዓመታት አከባበሩ ደብዝዟል።አከባበሩ መደብዘዙ አደጋ መሆኑን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የካቲት 12/2011 ዓም ባቀረበው የምሽት ዜና እወጃ ላይ የታሪክ ባለሙያዎችንም አነጋግሮ አረጋግጧል።

በኢትዮጵያም እስከ 1968 ዓም ድረስ የየካቲት 12 የሰማዕታት ቀን ትምህርት ቤቶች ሻማ በማብራት በሕበረት በመዘከር በመላ የሀገሪቱ ክፍል ዘክረው ይውሉ ነበር። በመንግስት መስርያቤትም በከፍተኛ ደረጃ ተከብሮ ይውል ነበር።በ1968 ዓም በዓሉ አከባበሩ ዝቅ ብሎ ታስቦ ብቻ እንዲውል ያደረገው የደርግ መንግስት ነው።ከደርግ ዘመን በኃላ ላለፉት 28 ዓመታት በባሰ መልኩ በዓሉ የመገናኛ ብዙኃንን ሽፋን ሳይቀር በበቂ መልኩ ሳያገኝ ቀርቷል። ይህ በእራሱ ብሔራዊ አደጋ ነው።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 12 ብሔራዊ የሰማዕታቱ የመታሰቢያ ቀን ሆኖ በብሔራዊ ደረጃ አከባበሩም ሕግ እና ስርዓት ወጥተውለት በመላዋ ኢትዮጵያ በአዋጅ እንዲከበር እንዲያደርግ ይህንን ፊርማ ማሰባሰብ አስፈላጊ ሆኗል።

የበዓሉ በብሔራዊ ደረጃ የመከበሩ ፋይዳ የአዲስ አበባ ከተማ እጅግ አሰቃቂ ውጣ ውረድ አልፋ እዚህ መድረሷን ብቻ የሚያሳይ ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ዘር፣ቋንቋ እና ኃይማኖት ሳይለያያቸው በደም በተለወሰ መስዋዕትነት የገነቧት ሀገር መሆኗን ለትውልዱ የማስተማርያ አይነተኛ መንገድ ነው።

ስለሆነም ይህንን ፊርማ በመፈረም እና ላልሰሙም በማካፈል ኃላፊነትዎን ይወጡ!

የካቲት 12 ሰላሳ ሺህ ኢትዮጵያውያን የሞቱበት የሰማዕታት ቀን በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበር የተወካዮች ምክር ቤት እንዲወስን ፊርማዎን እንዲያሳርፉ በሰማዕታቱ ስም ይለመናሉ።

ጉዳያችን / Gudayachn