Petition Closed

AKLESIA አቅሌስያ (ቤተ ክርስቲያን)

This petition had 5,250 supporters


በእንተ አቅሌስያ (ቤተ ክርስቲያን)

የሕግጋት ሁሉ ባለቤት በሆነው በልዑል እግዚአብሔር አጋዥነት የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባለው መንፈሳዊ ሥልጣን መሠረት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ለልጆቿ ጠባቂ የሚሆኑላትን አበው ጳጳሳት በመንፈስ ቅዱስና በፍትሕ መንፈሳዊ በመታገዝ ይሾምልን ዘንድ ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን (ፍትሐ ነገሥት) ያዛል።

የስርዓተ መጽሐፋችን "ኤጲስ ቆጶስ በሚሾምበት ቀን ሰዎች ሁሉ ይገኙ። ሕዝብና ካህናት መስክረውለት ይሾም።..."ፍትሐ ነገሥት በእንተ ኤጲስ ቆጶሳት ፤ አንቀጽ ፭፡፻፩ እንዲል እኛም ይሄንኑ መሠረት በማድረግ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የምንኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች የሆንን በሙሉ ከፊታችን በሚመጣው ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በመሠረት በጵጵስና ሊሾሙ ከታጩት 16 አባቶች መካከል የአባ ኃይለ ማርያም ዶ/ር እና የአባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ የጵጵስና ሹመታቸውን አጥብቀን በመቃውም! የተቃውሞ ፊርማችንን ለቅዱስ ሲኖዶስ እናቀርባለን።

ቡራኬው የማይደርሰንን ጳጳስ አትሹሙብን!!Today: AKELSIA is counting on you

AKELSIA አቅሌስያ (ቤተ ክርስቲያን ) needs your help with “ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ: አቅሌስያ (ቤተ ክርስቲያን)”. Join AKELSIA and 5,249 supporters today.