ለአዲስአበባ ነዋሪ የህግ ምሩቃን ተማሪዎች የቅድመ ስራ ስልጠና መስጫ ተቋም ይከፈት

ለአዲስአበባ ነዋሪ የህግ ምሩቃን ተማሪዎች የቅድመ ስራ ስልጠና መስጫ ተቋም ይከፈት

Started
September 14, 2022
Signatures: 241Next Goal: 500
Support now

Why this petition matters

የአዲስ አበባ የህግ ምሩቃንን ያገለለው የስልጠና እና ስራ ዕድል

የኢትዮጵያ ፍትህ ስርዓት አዳዲስ የህግ ምሩቃንን በዳኝት እና በዐቃቤ ህግነት አሰልጥኖ የሚቀጥር ነው። የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ሰልጣኞች በቀጥታ የፍትህ ስርዓቱን ከመቀላቀላቸው በፊት የተግባር ልምምድ እንዲያገኙ ማስቻል ነው። 

 

የ አዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ተመራቂዎች  “በአዲስ አበባ የፍትህ አካላት የቅድመ ስራ ስልጠና ተቋም ባለመኖሩ ዓቃቤ ህግ ወይም ዳኛ ሆነው ለመሥራት መቸገራቸውን ይናገራሉ። ወደ ክልልሎች ሲሄዱም ስልጠና ለማግኘት የነዋሪነት መታወቂያና ቋንቋ እንደ ቅድመ ሁኔታ በመቀመጡ ስልጠናውን ማግኘት ሳይችሉ ይቀራሉ።

በተጨማሪም ከክልሉ ነዋሪ ውጪ እድሉን እንደማይሰጡና ቅድሚያ ለክልሎቹ ተመራቂዎች እንደሆነም ይነገራቸዋል።

 

የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ "አዲስ አበባ የራሷ የሆነ የፍትሕ አካላት ማሰልጠኛ ተቋም ባይኖራትም ከፌደራል የፍትህ እና የህግ ምርምር ተቋም በመቀናጀት ስልጠናው እየሰጠን መጥተናል፣ አሁንም እንሰጣለን። በመሆኑም ተቋም አለመኖሩ ችግር የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም” ባይ ናቸው። ከተማዋ የራሷ የሆነ የፍትህ አካላት የቅድመ ሥራ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲኖራት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

 

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ  የህግ ባለሙያ “አንድ የህግ ባለሙያ  ስልጠና ካልወሰደና በዓቃቤ ህግነት ወይም በዳኝነት ተቀጥሮ የመስራት አድሉ ጠባብ ነው ለዚህ ችግር መፍትሄው  አዲስ አበባ የራሷ የሆነ የህግ የቅድመ ስልጠና ማዕከል ማቋቋም ወይም እንኳን አዲስ አበባ የፌደራል መንግስት መቀመጫ እስከሆነች ድረስ ነዋሪዎቿ በፌደራል የፍትህ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ገብተው ስልጠናውን እንዲወስዱ ሊፈቀድላቸው ይገባል" ብለዋል።

 

Support now
Signatures: 241Next Goal: 500
Support now
to help others easily find and sign the petition.